Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 20:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 ምል​ክ​ቱም በጢሱ ዐምድ ከከ​ተ​ማው ሊወጣ በጀ​መረ ጊዜ ብን​ያ​ማ​ው​ያን ወደ​ኋ​ላ​ቸው ተመ​ለ​ከቱ፤ እነ​ሆም፥ የሞላ ከተ​ማው ጥፋት ወደ ሰማይ ወጣ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 ነገር ግን የጢሱ ዐምድ ከከተማዪቱ መነሣት በጀመረ ጊዜ፣ ብንያማውያን ወደ ኋላቸው ዞረው የመላዪቱ ከተማ ጢስ ወደ ሰማይ ሲወጣ አዩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 ነገር ግን የጢሱ ዐምድ ከከተማይቱ መነሣት በጀመረ ጊዜ፥ ብንያማውያን ወደ ኋላቸው ዞረው የመላይቱ ከተማ ጢስ ወደ ሰማይ ሲወጣ አዩ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 ከዚህም በኋላ ምልክቱ ታየ፤ ይኸውም ጢሱ እንደ ደመና ሆኖ እየተትጐለጐለ ወደ ላይ ይወጣ ነበር፤ ብንያማውያንም ወደኋላቸው ሲመለከቱ ከተማይቱ በሙሉ በእሳት ተያይዛ ነበልባሉ ወደ ላይ ሲወጣ አዩ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 ምልክቱ በጢሱ ዓምድ ከከተማው ሊወጣ በጀመረ ጊዜ ብንያማውያን ወደ ኋላቸው ተመለከቱ፥ እነሆም፥ የሞላ ከተማው ጥፋት ወደ ሰማይ ወጣ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 20:40
6 Referencias Cruzadas  

ወደ ሰዶ​ምና ገሞራ፥ ወደ አው​ራ​ጃ​ዎ​ች​ዋም ሁሉ ተመ​ለ​ከተ፤ እነ​ሆም፥ ነበ​ል​ባል ከም​ድር እንደ ምድጃ ጢስ ሲወጣ አየ።


መዓ​ዛዋ እንደ ከር​ቤና እንደ ዕጣን የሆ​ነው፥ ከልዩ የሽቱ ቅመም ሁሉ የሆ​ነው፥ ይህች ከም​ድረ በዳ እንደ ጢስ ዐምድ የወ​ጣ​ችው ማን ናት?


በላይ በሰ​ማይ ድን​ቆ​ችን አሳ​ያ​ለሁ፤ በታች በም​ድ​ርም ደምና እሳት የጢ​ስም ጭጋግ።


የጋ​ይም ሰዎች ወደ ኋላ​ቸው ዞረው በተ​መ​ለ​ከቱ ጊዜ የከ​ተ​ማ​ዪቱ ጢስ ወደ ሰማይ ሲወጣ አዩ፤ ወዲ​ህና ወዲያ መሸሽ አል​ቻ​ሉም፤ ወደ ምድረ በዳም የሸሹ ሕዝብ በሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​አ​ቸው ላይ ተመ​ለሱ።


ደግመውም “ሃሌ ሉያ! ጢስዋም ለዘላለም እስከ ዘላለም ይወጣል፤” አሉ።


እነ​ሆም አንድ ሽማ​ግሌ ከእ​ር​ሻው ሥራ ወደ ማታ መጣ፤ ይህም ሰው ከተ​ራ​ራ​ማው ከኤ​ፍ​ሬም ሀገር ነበረ፤ በገ​ባ​ዖ​ንም በእ​ን​ግ​ድ​ነት ተቀ​ምጦ ነበር፤ የዚያ ሀገር ሰዎች ግን የብ​ን​ያም ልጆች ነበሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos