ኢያሱ 6:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀንደ መለከቱም ባለማቋረጥ ሲነፋ፥ የመለከቱን ድምፅ ስትሰሙ፥ ሕዝቡ ሁሉ ታላቅ ጩኸት ይጩኹ፤ የከተማዪቱም ቅጥር ይወድቃል፤ ሕዝቡም ሁሉ እያንዳንዱ ፊት ለፊት እየሮጠ ይገባባታል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የማያቋርጥ የመለከት ድምፅ ሲነፋ በምትሰሙበት ጊዜ፣ ሕዝቡ ሁሉ ከፍ ያለ ጩኸት ያሰማ፤ ከዚያም የከተማዪቱ ቅጥር ይፈርሳል፤ ሕዝቡም ወደ ላይ ይወጣል፤ እያንዳንዱም ሰው በቀጥታ ይገባል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀንደ መለከቱም ባለማቋረጥ ሲነፋ፥ የመለከቱን ድምፅ ስትሰሙ፥ ሕዝቡ ሁሉ ታላቅ ጩኸት ይጩኹ፤ የከተማይቱም ቅጥር ይወድቃል፥ ሕዝቡም ሁሉ እያንዳንዱ ወደ እርሷ አቅንቶ በቀጥታ ይገባል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያን በኋላ ካህናቱ በእምቢልታቸው ከፍተኛ ድምፅ እንዲሰማ ያድርጉ፤ እርሱንም እንደ ሰማችሁ ወዲያውኑ ሰዎቹ ሁሉ በከፍተኛ ድምፅ ይጩኹ፤ የከተማይቱም ቅጽር ይፈርሳል፤ ከዚህም በኋላ መላው ሠራዊት ወደ ከተማይቱ ሰተት ብሎ በቀጥታ ይግባ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቀንደ መለከቱም ባለማቋረጥ ሲነፋ፥ የመለከቱን ድምፅ ስትሰሙ፥ ሕዝቡ ሁሉ ታላቅ ጩኸት ይጩኹ፥ የከተማይቱም ቅጥር ይወድቃል፥ ሕዝቡም ሁሉ እያንዳንዱ አቅንቶ ይገባባታል። |
የተመሸገውንና ከፍ ከፍ ያለውንም ቅጥርህን ዝቅ ያደርገዋል። ያዋርደውማል፤ ወደ መሬትም እስከ አፈር ድረስ ይጥለዋል።
በታላቅም እልቂት ቀን ግንቦች በወደቁ ጊዜ፥ በረዥሙ ተራራ ሁሉ ከፍ ባለውም ኮረብታ ሁሉ ላይ፥ ወንዞችና የውኃ ፈሳሾች ይሆናሉ።
እጆችዋ ደክመዋልና ክበቡአት፤ ግንቧ ወድቋል፤ ቅጥርዋም ፈርሶአል፤ የእግዚአብሔርም በቀል ነውና ተበቀሏት፤ እንደ ሠራችውም ሥሩባት።
እንዲህም ሆነ፤ ከተማዪቱን ሰባት ጊዜ በዞሩና ካህናቱ ቀንደ መለከቱን በነፉ ጊዜ፤ ኢያሱ ለእስራኤል ልጆች አለ፥ “እግዚአብሔር ከተማዪቱን ሰጥቶአችኋልና ጩኹ።
ሕዝቡም ጮኹ፥ ካህናቱም ቀንደ መለከቱን ነፉ፤ ሕዝቡም የቀንደ መለከቱን ድምፅ በሰሙ ጊዜ ታላቅ ጩኸት ጮኹ፤ ቅጥሩም ወደቀ፤ ሕዝቡም ሁሉ ወደ ከተማዪቱ ገቡ፤ ሁሉም ወደ ፊታቸው ወደ ከተማዪቱ ሮጡ፤ ከተማዪቱንም እጅ አደረጉ።
ሰባትም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት በታቦቱ ፊት ይያዙ፤ በሰባተኛውም ቀን ከተማዪቱን ሰባት ጊዜ ዙሩ፤ ካህናቱም ቀንደ መለከቱን ይንፉ።
የነዌም ልጅ ኢያሱ ካህናቱን ጠርቶ፥ “የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸከሙ፤ ሰባትም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት ወስደው በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ይሂዱ” አላቸው።
ዳዊትም ማልዶ ተነሣ፤ በጎቹንም ለጠባቂ ተወ፤ እሴይም ያዘዘውን ይዞ ሄደ፤ ጭፍራውም ተሰልፎ ሲወጣ፥ ለሰልፍም ሲጮኽ በሰረገሎች ወደ ተከበበው ሰፈር መጣ።
የእስራኤልና የይሁዳ ሰዎችም ተነሥተው እልል አሉ፤ ፍልስጥኤማውያንንም እስከ ጌትና እስከ አስቀሎና በር ድረስ አሳደዱአቸው። የፍልስጥኤማውያንም በድኖቻቸው እስከ ጌትና እስከ አቃሮን በሮች ድረስ በመንገድ ላይ ወደቁ።
የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ሰፈር በገባች ጊዜ እስራኤል ሁሉ ታላቅ እልልታ አደረጉ፤ ምድሪቱም አስተጋባች።