La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 3:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ኢያ​ሱም ሕዝ​ቡን፥ “ነገ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ድንቅ ነገር ያደ​ር​ጋ​ልና ራሳ​ች​ሁን አንጹ” አለ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ኢያሱ ሕዝቡን፣ “በነገው ዕለት እግዚአብሔር በመካከላችሁ አስደናቂ ነገር ስለሚያደርግ ራሳችሁን ቀድሱ” አላቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኢያሱም ሕዝቡን፦ “ነገ ጌታ በመካከላችሁ ድንቅ ነገር ያደርጋልና ተቀደሱ” አለ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኢያሱም ሕዝቡን፦ “እግዚአብሔር ነገ በመካከላችሁ ተአምራትን ስለሚያደርግ ራሳችሁን አንጹ” አላቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኢያሱም ሕዝቡን፦ ነገ እግዚአብሔር በመካከላችሁ ድንቅ ነገር ያደርጋልና ተቀደሱ አለ።

Ver Capítulo



ኢያሱ 3:5
16 Referencias Cruzadas  

የግ​ብ​ዣ​ውም ቀኖች በተ​ፈ​ጸሙ ጊዜ ኢዮብ ይል​ክና ይቀ​ድ​ሳ​ቸው ነበር፤ በማ​ለ​ዳም ገሥ​ግሦ፦ ስለ ልጆቹ በቍ​ጥ​ራ​ቸው መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ርብ ነበር፤ አንድ ወይ​ፈን ስለ ነፍ​ሳ​ቸው የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ርብ ነበር፤ ኢዮብ፥ “ምና​ል​ባት ልጆቼ በል​ባ​ቸው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ክፉ ነገር ያስቡ ይሆ​ናል” ይል ነበ​ርና።


ዓለ​ቱን በም​ድረ በዳ ሰነ​ጠቀ፤ ከብዙ ጥልቅ እን​ደ​ሚ​ገኝ ያህል አጠ​ጣ​ቸው።


ሕዝ​ቡ​ንም ሰብ​ስቡ፤ ማኅ​በ​ሩ​ንም ቀድሱ፤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹ​ንም ጥሩ፤ ጡት የሚ​ጠ​ቡ​ት​ንና ሕፃ​ና​ትን ሰብ​ስቡ፤ ሙሽ​ራው ከእ​ል​ፍኙ፥ ሙሽ​ራ​ዪ​ቱም ከጫ​ጕ​ላዋ ይውጡ።


ሙሴም አሮ​ንን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ ወደ እኔ በሚ​ቀ​ርቡ እመ​ሰ​ገ​ና​ለሁ፤ በሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ፊት እከ​ብ​ራ​ለሁ ብሎ የተ​ና​ገ​ረው ይህ ነው” አለው፤ አሮ​ንም ደነ​ገጠ።


እን​ግ​ዲህ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ቅዱስ ነኝና ቅዱ​ሳን ሁኑ።


ሕዝ​ቡም እየ​ዞሩ ይለ​ቅሙ ነበር፤ በወ​ፍ​ጮም ይፈ​ጩት፥ ወይም በሙ​ቀጫ ይወ​ቅ​ጡት፥ በም​ን​ቸ​ትም ይቀ​ቅ​ሉት ነበር፤ እን​ጎ​ቻም ያደ​ር​ጉት ነበር፤ ጣዕ​ሙም በዘ​ይት እንደ ተለ​ወሰ እን​ጎቻ ነበረ።


እነ​ር​ሱም በእ​ው​ነት ቅዱ​ሳን ይሆኑ ዘንድ ስለ እነ​ርሱ እኔ ራሴን እቀ​ድ​ሳ​ለሁ።


እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ የም​ድ​ርን ሁሉ ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ካህ​ናት እግር ጫማ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ውኃ ውስጥ ሲቆም፥ የዮ​ር​ዳ​ኖስ ውኃ ይደ​ር​ቃል፤ ከላይ የሚ​ወ​ር​ደ​ውም ውኃ ይቆ​ማል።”


እንደ ክረ​ም​ትና እንደ መከር ወራት ሁሉ ዮር​ዳ​ኖስ እስከ ወሰኑ ሞልቶ ነበ​ርና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳን ታቦት ተሸ​ካ​ሚ​ዎቹ ወደ ዮር​ዳ​ኖስ በገቡ ጊዜ፥ ታቦ​ቱን የተ​ሸ​ከ​ሙት የካ​ህ​ናቱ እግ​ሮች በው​ኃዉ ዳር ሲጠ​ልቁ፥


በእ​ና​ን​ተና በታ​ቦቱ መካ​ከል ያለው ርቀት በስ​ፍር ሁለት ሺህ ክንድ ያህል ይሁን፤ በዚህ መን​ገድ በፊት አል​ሄ​ዳ​ች​ሁ​በ​ት​ምና የም​ት​ሄ​ዱ​በ​ትን መን​ገድ እን​ድ​ታ​ውቁ ወደ ታቦቱ አት​ቅ​ረቡ።”


ኢያ​ሱም ካህ​ና​ቱን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ተሸ​ክ​ማ​ችሁ በሕ​ዝቡ ፊት ሂዱ” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፤ ካህ​ና​ቱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ተሸ​ክ​መው በሕ​ዝቡ ፊት ሄዱ።


ተነ​ሣና ሕዝ​ቡን ቀድስ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ‘እስ​ራ​ኤል ሆይ! እርም የሆነ ነገር በመ​ካ​ከ​ልህ አለ፤ እር​ምም የሆ​ነ​ውን ነገር ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ እስ​ክ​ታ​ጠፉ ድረስ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችሁ ፊት መቆም አት​ች​ሉም’ ብሎ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሮ​አ​ልና እስከ ነገ ራሳ​ች​ሁን አንጹ።


እር​ሱም፥ “ለሰ​ላም ነው፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እሠዋ ዘንድ መጣሁ፤ ቅዱ​ሳን ሁኑ፤ ከእ​ኔም ጋር ዛሬ ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ ከእ​ኔም ጋር ወደ መሥ​ዋ​ዕቱ ኑ” አለ። እሴ​ይ​ንና ልጆ​ቹ​ንም ቀደ​ሳ​ቸው፤ ወደ መሥ​ዋ​ዕ​ቱም ጠራ​ቸው።