Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 11:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ሕዝ​ቡም እየ​ዞሩ ይለ​ቅሙ ነበር፤ በወ​ፍ​ጮም ይፈ​ጩት፥ ወይም በሙ​ቀጫ ይወ​ቅ​ጡት፥ በም​ን​ቸ​ትም ይቀ​ቅ​ሉት ነበር፤ እን​ጎ​ቻም ያደ​ር​ጉት ነበር፤ ጣዕ​ሙም በዘ​ይት እንደ ተለ​ወሰ እን​ጎቻ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ሕዝቡ ተዘዋውሮ በመልቀም በወፍጮ ከፈጨ ወይም በሙቀጫ ከወቀጠ በኋላ በምንቸት ይቀቅለው ወይም ይጋግረው ነበር፤ ጣዕሙም በወይራ ዘይት የተጋገረ ያህል ይጣፍጥ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ሕዝቡም እየዞሩ ይለቅሙ ነበር፥ በወፍጮም ይፈጩት፥ ወይም በሙቀጫ ይወቅጡት፥ በሸክላም ድስት ይቀቅሉት ነበር፥ እንጐቻም ያደርጉት ነበር፤ ጣዕሙም በዘይት እንደ ተለወሰ እንጐቻ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ሰዎቹም እየዞሩ ይለቅሙ ነበር፤ በወፍጮም ይፈጩት ወይም በሙቀጫ ይወቅጡት፥ በምንቸትም ያፈሉትና ይጋግሩት ነበር፤ ጣዕሙም በዘይት እንደ ተለወሰ ቂጣ ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ሕዝቡም እየዞሩ ይለቅሙ ነበር፥ በወፍጮም ይፈጩት፥ ወይም በሙቀጫ ይወቅጡት፥ በምንቸትም ይቀቅሉት ነበር፥ እንጐቻም ያደርጉት ነበር፤ ጣዕሙም በዘይት እንደ ተለወሰ እንጐቻ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 11:8
9 Referencias Cruzadas  

ለያ​ዕ​ቆ​ብም የም​ስር ንፍሮ ቀቀ​ለ​ች​ለት፤ ዔሳ​ውም ደክሞ ከበ​ረሃ ገባ፤


ሙሴም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረው ይህ ነው፦ ነገ ዕረ​ፍት፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ቀ​ደሰ ሰን​በት ነው፤ ነገ የም​ት​ጋ​ግ​ሩ​ትን ዛሬ ጋግሩ፤ የም​ት​ቀ​ቅ​ሉ​ት​ንም ቀቅሉ፤ የተ​ረ​ፈ​ው​ንም ሁሉ ለነገ እን​ዲ​ጠ​በቅ አኑሩ” አላ​ቸው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ስሙን መና ብለው ጠሩት፤ እር​ሱም እንደ ድን​ብ​ላል ዘር ነጭ ነው፤ ጣዕ​ሙም እንደ ማር እን​ጀራ ነው።


መና​ውም እንደ ድን​ብ​ላል ዘር ነበረ፤ መል​ኩም እንደ በረድ ነጭ ነበር።


ሌሊ​ትም ጠል በሰ​ፈሩ ላይ በወ​ረደ ጊዜ መናው በላዩ ይወ​ርድ ነበር።


የሰው ልጅ ለሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት ለሚ​ኖር መብል ሥሩ እንጂ ለሚ​ጠ​ፋው መብል አይ​ደ​ለም፤ ይህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ አት​ሞ​ታ​ልና።”


አባ​ቶ​ቻ​ች​ንስ ‘ሊበሉ እን​ጀራ ከሰ​ማይ ሰጣ​ቸው’ ተብሎ እንደ ተጻፈ በም​ድረ በዳ መና በሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos