ወንድማችሁን ያመጣ ዘንድ ከእናንተ አንዱን ላኩ፤ እናንተ ግን እውነትን የምትናገሩ ከሆነ ወይም ከአልሆነ ነገራችሁ እስኪታወቅ ድረስ ከዚህ ተቀመጡ፤ ይህ ከአልሆነ ‘የፈርዖንን ሕይወት!’ ሰላዮች ናችሁ።”
ኢያሱ 2:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የነዌም ልጅ ኢያሱ፥ “ውጡና ምድሪቱን ኢያሪኮን እዩ” ብሎ ከሰጢም ሁለት ጐልማሶች ሰላዮችን በስውር ላከ። እነዚያም ሁለት ጐልማሶች ሄዱ፤ ወደ ኢያሪኮም ደረሱ፤ ረዓብ ወደሚሉአትም ዘማ ቤት ገቡ፤ በዚያም ዐደሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የነዌ ልጅ ኢያሱ፣ “ሄዳችሁ ምድሪቱን፣ በተለይም የኢያሪኮን ከተማ ሰልሉ” ብሎ ከሰጢም ሁለት ሰላዮች በስውር ላከ፤ ሰዎቹም ሄደው ረዓብ ከተባለች ጋለሞታ ቤት ገቡ፤ በዚያም ዐደሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የነዌም ልጅ ኢያሱ ከሰጢም ሁለት ሰላዮች በስውር እንዲህ ብሎ ላከ፦ “ሄዱ፥ ምድሪቱንና ኢያሪኮን እዩ።” ሄዱም፤ ረዓብም ወደሚሉአት አመንዝራ ቤት ገቡ፥ በዚያም አደሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ የነዌ ልጅ ኢያሱ ከሺጢም ሰፈር ሁለት ሰላዮችን ላከ፤ እነርሱም የከነዓንን ምድር በተለይም የኢያሪኮን ከተማ በምሥጢር ሰልለው እንዲመለሱ አዘዛቸው፤ ወደ ከተማይቱ በመጡ ጊዜ “ረዓብ” ተብላ ወደምትጠራ ወደ አንዲት ሴትኛ ዐዳሪ ቤት ገብተው ዐደሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የነዌም ልጅ ኢያሱ፦ ሄዳችሁ ምድሪቱንና ኢያሪኮን እዩ ብሎ ከሰጢም ሁለት ሰላዮች በስውር ላከ። ሄዱም፥ ረዓብም ወደሚሉአት ጋለሞታ ቤት ገቡ፥ በዚያም አደሩ። |
ወንድማችሁን ያመጣ ዘንድ ከእናንተ አንዱን ላኩ፤ እናንተ ግን እውነትን የምትናገሩ ከሆነ ወይም ከአልሆነ ነገራችሁ እስኪታወቅ ድረስ ከዚህ ተቀመጡ፤ ይህ ከአልሆነ ‘የፈርዖንን ሕይወት!’ ሰላዮች ናችሁ።”
ሕዝቤ ሆይ፥ የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ የመከረውን፥ የቢዖርም ልጅ በለዓም የመለሰለትን አሁን አስብ፥ የእግዚአብሔርንም የጽድቅ ሥራ ታውቅ ዘንድ ከሰጢም ጀምሮ እስከ ጌልገላ ድረስ አስብ።
“ይገዙአት ዘንድ እኔ ለእስራኤል ልጆች የምሰጣትን የከነዓንን ምድር የሚሰልሉ ሰዎችን ላክ፤ ከአባቶች ቤት ከእያንዳንዱ ነገድ ሁሉ በመካከላቸው አለቃ የሆነ አንድ አንድ ሰው ትልካላችሁ።”
ሴሰኛ፥ ወይም ኀጢአተኛ፥ ወይም ቀማኛ፥ ወይም ጣዖትን የሚያመልክ ሁሉ በእግዚአብሔር ልጅ በክርስቶስ መንግሥት ዕድል ፋንታ እንደሌለው ይህን ዕወቁ።
የእስራኤልም ልጆች በጌልገላ ሰፈሩ፤ ከወሩም በዐሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በዮርዳኖስ ማዶ በኢያሪኮ ምዕራብ ፋሲካን አደረጉ።
የሌሳን ምድር ሊሰልሉ ሄደው የነበሩት አምስቱ ሰዎችም ወንድሞቻቸውን፥ “በእነዚህ ቤቶች ውስጥ ኢፉድና ተራፊም፥ የተቀረፀ ምስልና ቀልጦ የተሠራ ምስልም እንዳሉ ታውቃላችሁን?፤ አሁንም የምታደርጉትን ዕወቁ” ብለው ተናገሩአቸው።
ምድሪቱንም ሊሰልሉ ሄደው የነበሩት አምስቱ ሰዎች መጥተው ወደዚያ ገቡ፤ የተቀረፀውንም ምስል ኤፉዱንም፥ ተራፊሙንም ቀልጦ የተሠራውን ምስልም ወሰዱ፤ ካህኑም የጦር ዕቃ ከታጠቁት ከስድስት መቶ ሰዎች ጋር በደጃፉ አጠገብ ቆሞ ነበር።
የዳንም ልጆች ከወገናቸው አምስት ጽኑዓን ሰዎች ምድሪቱን እንዲሰልሉና እንዲመረምሩ፥ “ሂዱ ምድሪቱንም ሰልሉ” ብለው ከሶራሕና ከኢስታሔል ላኩ። እነዚያም ወደ ተራራማዉ ወደ ኤፍሬም ሀገር ወደ ሚካ ቤት መጥተው በዚያ አደሩ።