ኢያሱ 19:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተመሸጉትም የሲዶና ከተሞች እነዚህ ነበሩ፤ ጤሮስ፥ አማታዳቄት፥ ቄሬት፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተመሸጉትም ከተሞች እነዚህ ናቸው፤ ጺዲም፣ ጼር፣ ሐማት፣ ረቃት፣ ኬኔሬት፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የተመሸጉትም ከተሞች እነዚህ ነበሩ፤ ጺዲም፥ ጼር፥ ሐማት፥ ረቃት፥ ኬኔሬት፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም የተመሸጉት ከተሞች ጺዲም፥ ጼር፥ ሐማት፥ ራቃት፥ የገሊላ ባሕር፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተመሸጉትም ከተሞች እነዚህ ነበሩ፥ ጺዲም፥ ጼር፥ ሐማት፥ |
በዚያም ዘመን ሰሎሞን፥ ከእርሱም ጋር እስራኤል ሁሉ ከኤማት መግቢያ ጀምሮ እስከ ግብፅ ወንዝ ድረስ ያለው ታላቅ ጉባኤ፥ እርሱ በሠራው ቤት ውስጥ በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት እየበሉና እየጠጡ፥ ደስታም እያደረጉ ሰባት ቀን በዓሉን አከበሩ።
በእስራኤልም ንጉሥ በፋቁሔ ዘመን የአሶር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር መጣ፤ ኢዮንና አቤልቤትመዓካን፥ ያኖዋንም፥ ቃዴስንና አሶርንም፥ ገለዓድንና ገሊላንም፥ የንፍታሌምንም ሀገር ሁሉ ወሰደ፤ ወደ አሶርም አፈለሳቸው።
ከመካናራ ወሰን ከፈስጋ ተራራ በታች ወደ ምሥራቅ እስከ ዓረባ ባሕር እርሱም የጨው ባሕር ድረስ ዓረባን፥ ዮርዳኖስንም ሰጠኋቸው።
በሸለቆውም ቤትሀራም፥ ቤትንምራ፥ ሱኮት፥ ጻፎን፥ የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎን መንግሥት ቅሬታ ነበረ። ድንበሩም ዮርዳኖስና በምሥራቅ በኩል ባለው በዮርዳኖስ ማዶ የኬኔሬት ባሕር ወዲያኛው ዳርቻ ነበረ።
ድንበሩም ወደ ምዕራብ ወደ አዝኖትታቦር ይዞራል፤ ከዚያም ወደ ያቃና ይወጣል፤ ከዚያም በደቡብ በኩል ወደ ዛብሎን፤ በምዕራብ በኩል ወደ አሴር፥ በዮርዳኖስም በፀሐይ መውጫ ወደ ይሁዳ ይደርሳል።
በንፍታሌም ባለው በተራራማው ሀገር በገሊላ ቃዴስን፥ በኤፍሬምም ባለው በተራራማው ሀገር ሴኬምን፥ በይሁዳም ባለው በተራራማው ሀገር ኬብሮን የምትባለውን የአርቦቅን ከተማ ለዩ።
ከንፍታሌምም ነገድ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን በገሊላ ውስጥ ቃዴስንና መሰማርያዋን፥ ኤማትንና መሰማርያዋን፥ ቃርቴንንና መሰማሪያዋን፤ ሦስቱን ከተሞች ሰጡአቸው።
ዲቦራም ልካ ከቃዴስ ንፍታሌም የአቢኒሔምን ልጅ ባርቅን ጠርታ እንዲህ አለችው፥ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ያዘዘህ አይደለምን? ሄደህ ወደ ታቦር ተራራ ውጣ፤ ከአንተም ጋር ከንፍታሌምና ከዛብሎን ልጆች ዐሥር ሺህ ሰዎች ውሰድ፤