በዚያም ተራራ ላይ የተቀመጡ ዐማሌቃዊና ከነዓናዊ ወረዱ፤ መትተዋቸውም እስከ ኤርማ ድረስ አሳደዱአቸው። ወደ ከተማም ተመለሱ።
ኢያሱ 15:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤለቦሂዳድ፥ ቤቴልና ኤርማም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤልቶላድ፣ ኪሲል፣ ሖርማ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤልቶላድ፥ ኪሲል፥ ሔርማ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤልቶላድ፥ ከሲል፥ ሖርማ፥ |
በዚያም ተራራ ላይ የተቀመጡ ዐማሌቃዊና ከነዓናዊ ወረዱ፤ መትተዋቸውም እስከ ኤርማ ድረስ አሳደዱአቸው። ወደ ከተማም ተመለሱ።
እግዚአብሔርም የእስራኤልን ድምፅ ሰማ፤ ከነዓናውያንንም አሳልፎ በእጃቸው ሰጣቸው፤ እነርሱንም፥ ከተሞቻቸውንም ሕርም ብለው አጠፉአቸው፤ የዚያን ስፍራ ስም “ሕርም” ብለው ጠሩት።
በዚያም ተራራማ አገር ይኖሩ የነበሩ አሞሬዎናውያን ወጥተው ተጋጠሙአችሁ፤ ንብ እንደምትነድፍም ነደፉአችሁ፤ አሳደዱአችሁም፤ ከሴይር እስከ ሔርማም ድረስ መቱአችሁ።
ይሁዳም ከወንድሙ ከስምዖን ጋር ሄደ፤ በሴፌት የተቀመጡትንም ከነዓናውያንን መቱ፤ ፈጽመውም አጠፉአት፤ የከተማዪቱንም ስም ሕርም ብለው ጠሩአት።