La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 13:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በሸ​ለ​ቆ​ውም ቤት​ሀ​ራም፥ ቤት​ን​ምራ፥ ሱኮት፥ ጻፎን፥ የሐ​ሴ​ቦን ንጉሥ የሴ​ዎን መን​ግ​ሥት ቅሬታ ነበረ። ድን​በ​ሩም ዮር​ዳ​ኖ​ስና በም​ሥ​ራቅ በኩል ባለው በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ የኬ​ኔ​ሬት ባሕር ወዲ​ያ​ኛው ዳርቻ ነበረ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በሸለቆው ውስጥ ደግሞ ቤትሀራምን፣ ቤትኒምራን፣ ሱኮትን፣ ዳፎንንና እስከ ኪኔሬት ባሕር ጫፍ የሚደርሰውን ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ያለውን ቀሪውን የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎንን ግዛት ያካትታል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በሸለቆውም ቤትሀራም፥ ቤትኒምራ፥ ሱኮት፥ ጻፎን፥ የተቀረውም የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎን መንግሥት ነበረ። ድንበሩም ዮርዳኖስና በምሥራቅ በኩል ባለው በዮርዳኖስ ማዶ የኪኔሬት ባሕር ወዲያኛው ዳርቻ ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዮርዳኖስ ሸለቆ በተለይ የሐሴቦን ንጉሥ የሲሖን መንግሥት ቅሬታ የሆኑትን ቤትሐራም፥ ቤትኒምራ፥ ሱኮትና ጻፎን ተብለው የሚጠሩትን ጭምር ያጠቃልላል፤ በምዕራብ በኩል የሚዋሰናቸውም የዮርዳኖስ ወንዝ ሲሆን፥ በሰሜን እስከ ገሊላ ባሕር ይደርሳል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በሸለቆውም ቤትሀራም፥ ቤትኒምራ፥ ሱኮት፥ ጻፎን፥ የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎን መንግሥት ቅሬታ ነበረ። ድንበሩም ዮርዳኖስና በምሥራቅ በኩል ባለው በዮርዳኖስ ማዶ የኪኔሬት ባሕር ወዲያኛው ዳርቻ ነበር።

Ver Capítulo



ኢያሱ 13:27
14 Referencias Cruzadas  

ያዕ​ቆብ ግን በሰ​ፈሩ አደረ፤ በዚ​ያም ለእ​ርሱ ቤትን ሠራ፤ ለከ​ብ​ቶ​ቹም ዳሶ​ችን አደ​ረገ፤ ስለ​ዚ​ህም የዚ​ያን ቦታ ስም ማኅ​ደር ብሎ ጠራው።


በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ሜዳ በሱ​ኮ​ትና በተ​ር​ታን መካ​ከል ባለው በወ​ፍ​ራሙ መሬት ውስጥ አስ​ፈ​ሰ​ሰው።


ለን​ጉሥ ከቀን በላይ ቀንን ትጨ​ም​ራ​ለህ፥ ዓመ​ታ​ቱም ከት​ው​ልድ ወደ ትው​ልድ ይሆ​ናሉ።


“አጣ​ሮት፥ ዲቦን፥ ያዜር፥ ነምራ፥ ሐሴ​ቦን፥ ኤል​ያሌ፥ ሲባማ፥ ናባው፥ ቤያን፤


ናም​ራን፥ ቤታ​ራ​ንን ሰባት የተ​መ​ሸጉ ከተ​ሞች አድ​ር​ገው ሠሩ፤ አስ​ረ​ዘ​ሙ​አ​ቸ​ውም፤ የበ​ጎች በረ​ቶ​ች​ንም ሠሩ።


ዳር​ቻ​ውም ከሴ​ፋማ በዐ​ይን ምሥ​ራቅ ወዳ​ለው ወደ አር​ቤላ ይወ​ር​ዳል፤ እስከ ኬኔ​ሬት የባ​ሕር ወሽ​መጥ በም​ሥ​ራቅ በኩል ይደ​ር​ሳል፤


ብዙ ሰዎ​ችም በእ​ርሱ ዘንድ ነበሩ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ይሰሙ ነበር፤ እርሱ ግን በጌ​ን​ሴ​ሬጥ ባሕር ወደብ ቁሞ ነበር።


ከመ​ካ​ናራ ወሰን ከፈ​ስጋ ተራራ በታች ወደ ምሥ​ራቅ እስከ ዓረባ ባሕር እር​ሱም የጨው ባሕር ድረስ ዓረ​ባን፥ ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም ሰጠ​ኋ​ቸው።


በመ​ስ​ዕም በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር ፥ በከ​ነ​ሬ​ትም ዐዜብ በዓ​ረባ፥ በቆ​ላ​ውም ባለ በፊ​ና​ዶር ሸለቆ ወደ ነበሩ ነገ​ሥ​ታት፥


በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል ያለ​ውን ዓረባ እስከ ኬኔ​ሬት ባሕር ድረስ፥ በአ​ሴ​ሞት መን​ገድ አጠ​ገብ እስ​ካ​ለው እስከ ዓረባ ባሕር እስከ ጨው ባሕር ድረስ፥ በደ​ቡ​ብም በኩል ከፋ​ስጋ ተራራ አፋፍ በታች ያለ​ውን ምድር የገ​ዛው የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ንጉሥ ሴዎን፤


ከሐ​ሴ​ቦን ጀምሮ እስከ አራ​ቦት መሴፋ፥ እስከ ቦጣ​ኒም ድረስ፥ ከማ​ኦን ጀምሮ እስከ ዴቦን ዳርቻ ድረስ፥


የጋድ ልጆች ርስት ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም፥ መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ይህ ነበረ። በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ፊት ጀር​ባ​ቸ​ውን መል​ሰው ሸሹ፤ መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸ​ውና ከተ​ሞ​ቻ​ቸው በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ሆነ​ዋ​ልና።