በእውነት የተራሮች ኀይል፥ የኮረብቶችም ኀይል ሐሰት ነው፤ ነገር ግን የእስራኤል መዳን በአምላካችን በእግዚአብሔር ዘንድ ነው።
ኢያሱ 11:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያ ጊዜም ኢያሱ ሄደ፤ በተራራማውም ሀገር የሚኖሩ ኤናቃውያንን ከኬብሮንና ከዳቤር፥ ከአናቦትም፥ ከእስራኤልም ተራራ ሁሉ፥ ከይሁዳም ተራራ ሁሉ አጠፋቸው፤ ኢያሱም ከከተሞቻቸው ጋር ፈጽሞ አጠፋቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ ኢያሱ ሄዶ በተራራማው አገር፣ ማለት በኬብሮን፣ በዳቤርና በዓናብ እንዲሁም በመላው የይሁዳና የእስራኤል ተራራማ አገሮች ያሉትን የዔናቅን ዘሮች ከነከተሞቻቸው በሙሉ ደመሰሳቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜም ኢያሱ መጣ፥ ከተራራማውም አገር ከኬብሮንም ከዳቤርም ከአናብም ከእስራኤልም ተራራማ ሁሉ ከይሁዳም ተራራማ ሁሉ የዔናቅን ልጆች ገደለ፤ ኢያሱም ከከተሞቻቸው ጋር ፈጽሞ አጠፋቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህን ጊዜ ዘምቶ ረጃጅሞች የሆኑትን የዐናቅን ዘሮች ደመሰሰ፤ እነርሱም በኮረብታማው አገር በኬብሮን፥ በደቢር፥ በዐናብ፥ በይሁዳና በእስራኤል ኮረብታማ አገሮች የሚኖሩ ነበሩ። ኢያሱ እነዚህን ሕዝቦችና ከተሞቻቸውን ሁሉ ደመሰሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜም ኢያሱ መጣ፥ ከተራራማውም አገር ከኬብሮንም ከዳቤርም ከአናብም ከእስራኤልም ተራራማ ሁሉ ከይሁዳም ተራራማ ሁሉ የዔናቅን ልጆች ገደለ፥ ኢያሱም ከከተሞቻቸው ጋር ፈጽሞ አጠፋቸው። |
በእውነት የተራሮች ኀይል፥ የኮረብቶችም ኀይል ሐሰት ነው፤ ነገር ግን የእስራኤል መዳን በአምላካችን በእግዚአብሔር ዘንድ ነው።
እኔ ግን ቁመቱ እንደ ዝግባ ቁመት፥ ብርታቱም እንደ ወይራ ዛፍ የነበረውን አሞራዊውን ከፊታቸው አጠፋሁ፤ ፍሬውንም ከላዩ፥ ሥሩንም ከታቹ አጠፋሁ።
በዚያም ግዙፋን የሆኑትን አየን፤ እኛም በእነርሱ ፊት እንደ አንበጣዎች ሆን፤ እንዲሁም በፊታቸው ነበርን፤” እያሉ የሰለሉአትን ምድር ለእስራኤል ልጆች አስፈሪ አደረጓት።
ወዴት እንወጣለን? ሕዝቡ ታላቅና ብዙ ነው፤ ከእኛም ይጠነክራሉ፤ ከተሞቹም ታላላቆች፥ የተመሸጉም፥ እስከ ሰማይም የደረሱ ናቸው፤ የረዐይትንም ልጆች ደግሞ በዚያ አየናቸው ብለው ወንድሞቻችን ልባችንን አስፈሩት።’
እነርሱም እንደ ዔናቃውያን ታላቅና ብዙ፥ ጽኑዓንም ሕዝብ ነበሩ፤ እግዚአብሔርም ከፊታቸው አጠፋቸው፤ እነርሱንም አሳድደው በስፍራቸው ተቀመጡ።
አንተም የምታውቃቸው፥ ስለ እነርሱም፦ በዔናቅ ልጆች ፊት መቆም ማን ይችላል? ሲባል የሰማኸው ታላቅ፥ ብዙና ረዥም ሕዝብ የዔናቅ ልጆች ናቸው።
የእስራኤልም አምላክ እግዚአብሔር ለእስራኤል ስለ ተዋጋላቸው ኢያሱ እነዚህን ነገሥታት ሁሉ ምድራቸውንም በአንድ ጊዜ ያዘ።
ሙሴም እንደ ተናገረ ለካሌብ ኬብሮንን ሰጡት፤ ከዚያም ሠላሳ ከተሞችን ወረሰ፤ ከዚያም ሦስቱን የዔናቅ ልጆች አስወገዳቸው።