ኢያሱ 11:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስከ ሴይርም ከሚያወጣው ከኤኬል ተራራ ጀምሮ ከአርሞንዔም ተራራ በታች እስከ ሊባኖስ ሜዳና እስከ በላጋድ ድረስ፤ ንጉሦቻቸውን ሁሉ ይዞ መታቸው፤ ገደላቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም እስከ ሴይር በሚደርሰው ከሐላቅ ተራራ አንሥቶ ከአርሞንዔም ተራራ በታች በሊባኖስ ሸለቆ ውስጥ እስካለው እስከ በኣልጋድ ድረስ ያለውን ምድር በሙሉ ያዘ፤ ነገሥታታቸውንም ሁሉ ያዘ፤ መትቶም ገደላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቈላውም እስከ ሴይር ከሚያወጣው ከሐላቅ ተራራ ጀምሮ ከአርሞንዔም ተራራ በታች በሊባኖስም ሸለቆ ውስጥ እስካለው እስከ በአልጋድ ድረስ ነበር፤ ነገሥታቶቻቸውንም ሁሉ ይዞ መታቸው፥ ገደላቸውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም ወደ ኤዶም ከሚያወጣው ከሐላቅ ተራራ ጀምሮ ከሔርሞን ተራራ በታች እስከ ሊባኖስ ሸለቆ እስከ ባዓልጋድ ድረስ ያሉትን ነገሥታት ሁሉ ማርኮ መታቸው፤ ገደላቸውም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስከ ሴይርም ከሚያወጣው ወና ከሆነው ተራራ ጀምሮ ከአርሞንዔም ተራራ በታች በሊባኖስም ሸለቆ ውስጥ እስካለው እስከ በአልጋድ ድረስ፥ ነገሥታቶቻቸውንም ሁሉ ይዞ መታቸው፥ ገደላቸውም። |
ተመልሳችሁ ተጓዙ፤ ወደ አሞራውያን ተራራ፥ ወደ አረባም ሀገሮች ሁሉ፥ በተራራውም፥ በሜዳውም፥ በሊባም፥ በባሕርም ዳር ወዳሉ ወደ ከነዓናውያን ምድር፥ ወደ ሊባኖስም ፊት ለፊት እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ድረስ ሂዱ።
“እግዚአብሔርም እንዳለኝ ተመልሰን በኤርትራ ባሕር መንገድ ወደ ምድረ በዳ ሄድን፤ የሴይርንም ተራራ ብዙ ቀን ዞርን።
እንዲህም አለ፦ “እግዚአብሔር ከሲና መጣ፤ በሴይርም ተገለጠልን፤ ከፋራን ተራራ፥ ከቃዴስ አእላፋት ጋር ፈጥኖ መጣ፤ መላእክቱም ከእርሱ ጋር በቀኙ ነበሩ።
ነገሥታቶቻቸውንም በእጅህ አሳልፎ ይሰጣቸዋል፤ ስማቸውንም ከዚያ ቦታ ያጠፋል፤ እስክታጠፋቸው ድረስ ማንም ከፊትህ ይቆም ዘንድ አይችልም።
ከሊባኖስ ፊት ለፊት ምድረ በዳ ጀምሮ እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ድረስ የኬጤዎናውያን ምድር ሁሉ እስከ ፀሐይ መግቢያ እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ወሰናችሁ ይሆናል።
በምሥራቃዊ ባሕር ዳርቻ ወዳለው ወደ ከነዓናዊው፥ ወደ አሞሬዎናዊውም፥ ወደ ኬጤዎናዊውም፥ ወደ ፌርዜዎናዊውም፥ በተራራማውም ሀገር ወዳለው ወደ ኢያቡሴዎናዊው፥ በቆላማውና በመሴፋ ወዳለው ወደ ኤዌዎናዊዉም ላከ።
በፍልስጥኤም ያለው የጌባላውያን ምድር ሁሉ፥ በምሥራቅም በኩል ከአርሞንዔም ተራራ በታች ካለችው ጌልገላ ጀምሮ እስከ ኤማት መግቢያ ድረስ ያለችው ሊባኖስ ሁሉ፥