ዘዳግም 7:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)24 ነገሥታቶቻቸውንም በእጅህ አሳልፎ ይሰጣቸዋል፤ ስማቸውንም ከዚያ ቦታ ያጠፋል፤ እስክታጠፋቸው ድረስ ማንም ከፊትህ ይቆም ዘንድ አይችልም። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም24 ነገሥታታቸውን በእጅህ ይጥላቸዋል፤ ስማቸውንም ከሰማይ በታች ታጠፋለህ። እስክትደመስሳቸው ድረስ አንተን መቋቋም የሚችል አንድም ሰው የለም። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)24 ነገሥታቶቻቸውንም በእጅህ አሳልፎ ይሰጣቸዋል፥ ስማቸውንም ከሰማይ በታች ታጠፋለህ፤ እስክታጠፋቸው ድረስ ማንም ተቋቁሞህ በፊት ሊቆም አይችልም። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም24 ንጉሦቻቸውን በእጅህ ይጥልልሃል፤ እነርሱንም ታጠፋና ስማቸው የተረሳ እንዲሆን ታደርጋለህ፤ ማንም ተቋቊሞ ሊገታህ አይችልም፤ ሁሉንም ታወድማለህ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)24 ነገሥታቶቻቸውንም በእጅህ አሳልፎ ይሰጣቸዋል፥ ስማቸውንም ከሰማይ በታች ታጠፋለህ፤ እስክታጠፋቸው ድረስ ማንም በፊትህ ይቆም ዘንድ አይችልም። Ver Capítulo |