ኤልያስም ያን በሰማ ጊዜ ፊቱን በመጐናጸፊያው ሸፈነ፤ ወጥቶም በዋሻው ደጃፍ ቆመ። እነሆም፥ “ኤልያስ ሆይ፥ ወደዚህ ለምን መጣህ?” የሚል ቃል ወደ እርሱ መጣ።
ዮናስ 4:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮናስም ከከተማዪቱ ወጣ፤ በከተማዪቱም ፊት ለፊት ተቀመጠ፤ በከተማዪቱም የሚሆነውን እስኪያይ ድረስ በዚያ ለራሱ ዳስ ሠርቶ ከጥላው በታች ተቀመጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮናስም ከከተማዪቱ ወጥቶ በስተምሥራቅ በአንድ ስፍራ ተቀመጠ። በዚያም ለራሱ ዳስ ሠራ፤ በከተማዪቱም የሚሆነውን ለማየት ከዳሱ ጥላ ሥር ተቀመጠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮናስም ከከተማይቱ ወጣ፥ ከከተማይቱም በስተ ምሥራቅ በኩል ተቀመጠ፥ ከተማይቱ የሚደርስባትን እስኪያይ ድረስ በዚያ ለራሱ ዳስ ሠራ፥ ከጥላዋ በታችም ተቀመጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮናስም ከከተማይቱ ወጥቶ ከከተማይቱም በስተ ምሥራቅ በኩል ዳስ በመሥራት ከጥላው ሥር ተቀመጠ፤ በዚያም ሆኖ በነነዌ ላይ የሚደርሰውን ነገር ይጠባበቅ ነበር። |
ኤልያስም ያን በሰማ ጊዜ ፊቱን በመጐናጸፊያው ሸፈነ፤ ወጥቶም በዋሻው ደጃፍ ቆመ። እነሆም፥ “ኤልያስ ሆይ፥ ወደዚህ ለምን መጣህ?” የሚል ቃል ወደ እርሱ መጣ።
እዚያም ወዳለ ዋሻ ገባ፤ በዚያም አደረ፤ እነሆም፥ “ኤልያስ ሆይ! ምን አመጣህ?” የሚል የእግዚአብሔር ቃል ወደ እርሱ መጣ።
እኔም እንዲህ አልሁ፥ “የእግዚአብሔርን ስም አላነሣም፤ ከእንግዲህ ወዲህ በስሙ አልናገርም፥” በአጥንቶች ውስጥ እንደ ገባ እንደሚነድድ እሳት ያለ በልቤ ሆነብኝ፤ ደከምሁ፤ መሸከምም አልቻልሁም።
መርከበኞቹም ፈሩ፤ እያንዳንዱም ወደ አምላኩ ጮኸ፤ መርከቢቱም እንድትቀልልላቸው በውስጥዋ የነበረውን ዕቃ ወደ ባሕር ጣሉት፤ ዮናስ ግን ወደ መርከቡ ውስጠኛው ክፍል ወርዶ ነበር፥ ተኝቶም ያንኳርፍ ነበር።
እግዚአብሔር አምላክም ቅልን አዘዘ፤ ከጭንቀቱም ታድነው ዘንድ በራሱ ላይ ጥላ እንድትሆን በዮናስ ራስ ላይ ከፍ ከፍ አደረጋት፤ ዮናስም ስለ ቅሊቱ እጅግ ደስ አለው።