አብርሃምም በማለዳ ተነሥቶ አህያውን ጫነ፤ ሁለቱንም ሎሌዎቹንና ልጁን ይስሐቅን ከእርሱ ጋር ወሰደ፤ ዕንጨትንም ለመሥዋዕት ሰነጠቀ፤ ተነሥቶም እግዚአብሔር ወዳለው ቦታ ሄደ፤ በሦስተኛውም ቀን ደረሰ።
ዮናስ 3:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮናስም ተነሥቶ እንደ እግዚአብሔር ቃል ወደ ነነዌ ሄደ፤ ነነዌም ታላቅ ከተማ ነበረች፤ የቅጥርዋም ዙሪያ በእግር የሦስት ቀን መንገድ ያህል ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮናስም የእግዚአብሔርን ቃል ታዘዘ፤ ወደ ነነዌም ሄደ። በዚህ ጊዜ ነነዌ ታላቅ ከተማ ነበረች፤ እርሷንም ከዳር እስከ ዳር ለመጐብኘት ሦስት ቀን ያስፈልግ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮናስም ተነሣና ጌታ እንደ ተናገረው ወደ ነነዌ ሄደ፤ ነነዌም እጅግ ታላቅ ከተማ ነበረች፥ ለማቋረጥም ሦስት ቀን ይፈጅ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮናስም ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ተነሥቶ ወደ ነነዌ ሄደ፤ ነነዌ እጅግ ታላቅ ከተማ ከመሆንዋ የተነሣ ከተማዋን በመላ ለማዳረስ ሦስት ቀን ይፈጅ ነበር። |
አብርሃምም በማለዳ ተነሥቶ አህያውን ጫነ፤ ሁለቱንም ሎሌዎቹንና ልጁን ይስሐቅን ከእርሱ ጋር ወሰደ፤ ዕንጨትንም ለመሥዋዕት ሰነጠቀ፤ ተነሥቶም እግዚአብሔር ወዳለው ቦታ ሄደ፤ በሦስተኛውም ቀን ደረሰ።
ራሔልም፥ “እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አደረገኝ፤ ብርቱ ትግልንም ከእኅቴ ጋር ታገልሁ፤ አሸነፍሁም፤ እኅቴንም መሰልኋት” አለች፤ ስሙንም ንፍታሌም ብላ ጠራችው።
እኔስ ቀኛቸውንና ግራቸውን የማይለዩ ከመቶ ሃያ ሺህ የሚበልጡ ሰዎችና ብዙ እንስሶች ላሉባት ለታላቂቱ ከተማ ለነነዌ አላዝንምን?” አለው።