Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዮናስ 3:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ዮናስም ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ተነሥቶ ወደ ነነዌ ሄደ፤ ነነዌ እጅግ ታላቅ ከተማ ከመሆንዋ የተነሣ ከተማዋን በመላ ለማዳረስ ሦስት ቀን ይፈጅ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ዮናስም የእግዚአብሔርን ቃል ታዘዘ፤ ወደ ነነዌም ሄደ። በዚህ ጊዜ ነነዌ ታላቅ ከተማ ነበረች፤ እርሷንም ከዳር እስከ ዳር ለመጐብኘት ሦስት ቀን ያስፈልግ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ዮናስም ተነሣና ጌታ እንደ ተናገረው ወደ ነነዌ ሄደ፤ ነነዌም እጅግ ታላቅ ከተማ ነበረች፥ ለማቋረጥም ሦስት ቀን ይፈጅ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ዮና​ስም ተነ​ሥቶ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ ነነዌ ሄደ፤ ነነ​ዌም ታላቅ ከተማ ነበ​ረች፤ የቅ​ጥ​ር​ዋም ዙሪያ በእ​ግር የሦ​ስት ቀን መን​ገድ ያህል ነበረ።

Ver Capítulo Copiar




ዮናስ 3:3
9 Referencias Cruzadas  

አብርሃም ጠዋት በማለዳ ተነሥቶ ለመሥዋዕቱ የሚሆን እንጨት ቈረጠና በአህያው ላይ ጫነው፤ ከእርሱ ጋር ልጁን ይስሐቅንና ሁለት አገልጋዮችን ይዞ እግዚአብሔር ወዳመለከተው ቦታ ለመሄድ ጒዞ ጀመረ።


ራሔልም “ከእኅቴ ጋር ብርቱ ትግል ታግዬ አሸነፍኳት” አለች፤ ስለዚህ ስሙን ንፍታሌም ብላ ጠራችው።


እግዚአብሔር ሆይ፥ ሰዎችንና እንስሶችን ከአደጋ ታድናለህ፤ ጽድቅህ እንደ ተራራዎች እጅግ ከፍ ያለ ነው፤ ፍርድህም እንደ ባሕር ጥልቅ ነው።


ጥላዋ ተራራዎችን የቅርንጫፎችዋም ጥላ የሊባኖስ ዛፎችን ሸፈነ።


ከዚህ በኋላ የአሦራውያን ንጉሥ ሰናክሬም ወደኋላው በማፈግፈግ ወደ ነነዌ ተመልሶ በዚያ ኖረ።


“ተነሥተህ ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ እኔ የሕዝብዋን ክፋት ተመልክቼአለሁ። ድምፅህንም ከፍ አድርገህ እርስዋን በመገሠጽ ተናገር።”


ነነዌ ክፉና ደጉን የማይለዩ ከአንድ መቶ ኻያ ሺህ ሕዝብ በላይ የሚኖሩባት ከተማ ነች፤ ብዙ እንስሶችም አሉባት፤ ታዲያ እኔ ለዚህች ታላቂቱ ከተማ አልራራምን?”


ከእኔ ጋር ያለው ሉቃስ ብቻ ነው፤ ማርቆስ ለአገልግሎት ስለሚጠቅመኝ ፈልገህ ይዘኸው ና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos