እግዚአብሔርን አልሁት፥ “አንተ አምላኬ ነህ፤ ለምን ረሳኸኝ? ጠላቶቼ ሲያስጨንቁኝ ለምን ተውኸኝ? ለምንስ አዝኜ እመለሳለሁ?” ጠላቶቼ ሁሉ አጥንቶቼን እየቀለጣጠሙ ሰደቡኝ።
ዮሐንስ 6:71 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህንም ስለ ስምዖን ልጅ ስለ አስቆሮታዊው ይሁዳ ተናገረ፤ እርሱ ያሲዘው ዘንድ አለውና፤ እርሱም ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአስቆሮቱ የስምዖን ልጅ ይሁዳ፣ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ቢሆንም፣ ኋላ አሳልፎ ስለሚሰጠው ስለ እርሱ መናገሩ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ስምዖን ልጅ ስለ አስቆሮቱ ይሁዳ መናገሩ ነበር፤ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ሲሆን፥ አሳልፎም የሚሰጠው እርሱ ነበርና ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም ያለው ስለ ስምዖን ልጅ ስለ አስቆሮታዊው ይሁዳ ነበር፤ ይሁዳ ምንም እንኳ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ቢሆን ኢየሱስን አሳልፎ የሚሰጥ እርሱ ስለ ነበር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ስምዖንም ልጅ ስለ አስቆሮቱ ይሁዳ ተናገረ፤ ከአሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነ እርሱ አሳልፎ ይሰጠው ዘንድ አለውና። |
እግዚአብሔርን አልሁት፥ “አንተ አምላኬ ነህ፤ ለምን ረሳኸኝ? ጠላቶቼ ሲያስጨንቁኝ ለምን ተውኸኝ? ለምንስ አዝኜ እመለሳለሁ?” ጠላቶቼ ሁሉ አጥንቶቼን እየቀለጣጠሙ ሰደቡኝ።
የዐሥራ ሁለቱም ሐዋርያት ስም ይህ ነው፤ መጀመሪያው ጴጥሮስ የተባለው ስምዖን ወንድሙ እንድርያስም፥ የዘብዴዎስ ልጅ ያዕቆብም ወንድሙ ዮሐንስም፥
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ፥ “ይህ እኔ እንጀራ በወጥ አጥቅሼ የምሰጠው ነው” አለው፤ ያን ጊዜም እንጀራ በወጥ አጥቅሶ ለስምዖን ልጅ ለአስቆሮታዊው ይሁዳ ሰጠው።
ነገር ግን ከእናንተ ውስጥ የማያምኑ አሉ፤” ጌታችን ኢየሱስ ከጥንት ጀምሮ የማያምኑበት እነማን እንደ ሆኑ፥ የሚያሲዘውም ማን እንደ ሆነ ያውቅ ነበርና።
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “እኔ እናንተን ዐሥራ ሁለታችሁን መርጫችሁ የለምን? ነገር ግን ከእናንተ አንዱ ሰይጣን ነው።”
እርሱንም በተወሰነው በእግዚአብሔር ምክርና በቀደመው ዕውቀቱ እናንተ አሳልፋችሁ በኃጥኣን እጅ ሰጣችሁት፤ ሰቅላችሁም ገደላችሁት።
ከብዙ ጊዜ በፊት ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንዶች ሰዎች ሾልከው ገብተዋልና፤ ኀጢአተኞች ሆነው የአምላካችንን ጸጋ በሴሰኝነት ይለውጣሉ፤ ብቻውን ንጉሣችንንና ጌታችንንም የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ።