Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዮሐንስ 6:71 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

71 የአስቆሮቱ የስምዖን ልጅ ይሁዳ፣ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ቢሆንም፣ ኋላ አሳልፎ ስለሚሰጠው ስለ እርሱ መናገሩ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

71 ስለ ስምዖን ልጅ ስለ አስቆሮቱ ይሁዳ መናገሩ ነበር፤ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ሲሆን፥ አሳልፎም የሚሰጠው እርሱ ነበርና ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

71 ይህንንም ያለው ስለ ስምዖን ልጅ ስለ አስቆሮታዊው ይሁዳ ነበር፤ ይሁዳ ምንም እንኳ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ቢሆን ኢየሱስን አሳልፎ የሚሰጥ እርሱ ስለ ነበር ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

71 ይህ​ንም ስለ ስም​ዖን ልጅ ስለ አስ​ቆ​ሮ​ታ​ዊው ይሁዳ ተና​ገረ፤ እርሱ ያሲ​ዘው ዘንድ አለ​ውና፤ እር​ሱም ከዐ​ሥራ ሁለቱ አንዱ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

71 ስለ ስምዖንም ልጅ ስለ አስቆሮቱ ይሁዳ ተናገረ፤ ከአሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነ እርሱ አሳልፎ ይሰጠው ዘንድ አለውና።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 6:71
19 Referencias Cruzadas  

ከረዥም ጊዜ በፊት ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንድ ሰዎች ሾልከው ወደ እናንተ ገብተዋልና፤ እነርሱ ፈሪሀ እግዚአብሔር የሌላቸው፣ የአምላካችንን ጸጋ በርኩሰት የሚለውጡና እርሱ ብቻ ልዑል ገዣችንና ጌታችን የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን የሚክዱ ናቸው።


እግዚአብሔር በጥንት ውሳኔውና በቀደመው ዕውቀቱ ይህን ሰው አሳልፎ በእጃችሁ ሰጣችሁ፤ እናንተም በክፉ ሰዎች እጅ ሰቅላችሁ ገደላችሁት።


ኢየሱስም፣ “ይህን ቍራሽ እንጀራ ከወጭቱ አጥቅሼ የምሰጠው እርሱ ነው” አለው፤ ከዚያም ቍራሹን እንጀራ አጥቅሶ ለስምዖን ልጅ ለአስቆሮቱ ይሁዳ ሰጠው።


እንጀራዬን የበላ፣ የምተማመንበትም የቅርብ ወዳጄ፣ ተረከዙን አነሣብኝ።


የዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ስም የሚከተለው ነው፤ መጀመሪያ ጴጥሮስ የተባለው ስምዖንና ወንድሙ እንድርያስ፣ የዘብዴዎስ ልጅ ያዕቆብና ወንድሙ ዮሐንስ፣


ቀነናዊው ስምዖንና በኋላ ኢየሱስን አሳልፎ የሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ።


ከዚህ በኋላ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ ሊሰጠው ወደ ካህናት አለቆች ሄደ።


ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰርጉ ተጠርተው ነበር።


ይሁን እንጂ ከእናንተ የማያምኑ አንዳንዶች አሉ።” ይህም፣ ኢየሱስ እነማን እንዳላመኑና ማን አሳልፎ እንደሚሰጠው ቀድሞውኑ ያውቅ ስለ ነበር ነው።


ኢየሱስም መልሶ፣ “ዐሥራ ሁለታችሁንም የመረጥኋችሁ እኔ አይደለሁምን? ነገር ግን ከእናንተ አንዱ ዲያብሎስ ነው!” አላቸው።


ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፣ ኋላ አሳልፎ የሚሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ ግን በመቃወም እንዲህ አለ፤


እራትም ቀርቦ ሳለ፣ ኢየሱስን አሳልፎ እንዲሰጥ ዲያብሎስ የስምዖንን ልጅ የአስቆሮቱን ይሁዳ ልብ አነሣሥቶ ነበር።


በዚህ ጊዜ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው፣ ዲዲሞስ የተባለው ቶማስ፣ ኢየሱስ በመጣ ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ አልነበረም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios