ዮሐንስ 6:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአይሁድ የፋሲካ በዓልም ቀርቦ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአይሁድ የፋሲካ በዓልም ተቃርቦ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአይሁድ በዓል ፋሲካም ቀርቦ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአይሁድ ፋሲካ በዓል ቀርቦ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአይሁድ በዓልም ፋሲካ ቀርቦ ነበር። |
የአይሁድም የፋሲካ በዓል ቀርቦ ነበር፤ ብዙ ሰዎችም ከበዓሉ አስቀድሞ ራሳቸውን ያነጹ ዘንድ ከየሀገሩ ወደ ኢየሩሳሌም ወጥተው ነበር።
ፋሲካ ከሚውልበት ከስድስተኛው ቀን አስቀድሞ ጌታችን ኢየሱስ ከሙታን ያስነሣው አልዓዛር ወደ ነበረበት ወደ ቢታንያ መጣ።
ከፋሲካ በዓል አስቀድሞ ጌታችን ኢየሱስ ከዚህ ዓለም ወደ ላከው ወደ አብ ይሄድ ዘንድ ጊዜው እንደ ደረሰ ባወቀ ጊዜ በዓለም ያሉትን የወደዳቸውን ወገኖቹን ፈጽሞ ወደዳቸው።
“በሚያዝያ ወር ከግብፅ ሀገር በሌሊት ወጥተሃልና የሚያዝያን ወር ጠብቀህ፥ የአምላክህ የእግዚአብሔርን ፋሲካ አድርግ።