La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዮሐንስ 20:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እነ​ዚያ መላ​እ​ክ​ትም፥ “አንቺ ሴት፥ ምን ያስ​ለ​ቅ​ስ​ሻል?” አሉ​አት፤ እር​ስ​ዋም፥ “ጌታ​ዬን ከመ​ቃ​ብር ውስጥ ወስ​ደ​ው​ታል፤ ወዴ​ትም እንደ ወሰ​ዱት አላ​ው​ቅም” አለ​ቻ​ቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነርሱም፣ “አንቺ ሴት፤ ለምን ታለቅሻለሽ?” ብለው ጠየቋት። እርሷም፣ “ጌታዬን ወስደውታል፤ የት እንዳኖሩትም አላውቅም” አለች።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነርሱም “አንቺ ሴት! ስለምን ታለቅሻለሽ?” አሉአት። እርሷም “ጌታዬን ወስደውታል፤ ወዴትም እንዳኖሩት አላውቅም፤” አለቻቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እነርሱም ማርያምን፥ “አንቺ ሴት! ለምን ታለቅሻለሽ?” አሉአት። እርስዋም “ጌታዬን ወስደውታል፤ የት እንዳደረጉትም አላውቅም” አለች።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነርሱም፦ “አንቺ ሴት፥ ስለ ምን ታለቅሻለሽ?” አሉአት። እርስዋም፦ “ጌታዬን ወስደውታል ወዴትም እንዳኖሩት አላውቅም” አለቻቸው።

Ver Capítulo



ዮሐንስ 20:13
13 Referencias Cruzadas  

ለማ​ል​ቀስ ጊዜ አለው፥ ለመ​ሣ​ቅም ጊዜ አለው፤ ዋይ ለማ​ለት ጊዜ አለው፥ ለመ​ዝ​ፈ​ንም ጊዜ አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ድም​ፅ​ሽን ከል​ቅሶ፥ ዐይ​ኖ​ች​ሽ​ንም ከእ​ንባ ከል​ክዪ፤ ለሥ​ራሽ ዋጋ ይሆ​ና​ልና፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ከጠ​ላ​ትም ምድር ይመ​ለ​ሳሉ።


ጌታ​ች​ንም፥ “በት​ካዜ እየ​ሄ​ዳ​ችሁ እርስ በር​ሳ​ችሁ የም​ት​ነ​ጋ​ገ​ሩት ይህ ነገር ምን​ድን ነው?” አላ​ቸው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እና​ቱ​ንና የሚ​ወ​ደ​ውን ደቀ መዝ​ሙ​ሩን ቆመው ባያ​ቸው ጊዜ እና​ቱን፥ “አንች ሆይ፥ እነሆ፥ ልጅሽ” አላት።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አንቺ ሆይ ካንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አል​ደ​ረ​ሰም” አላት።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አንቺ ሴት፥ ምን ያስ​ለ​ቅ​ስ​ሻል? ማን​ንስ ትሺ​ያ​ለሽ?” አላት፤ እር​ስዋ ግን የአ​ት​ክ​ልት ቦታ ጠባቂ መስ​ሎ​አት፥ “ጌታዬ፥ አንተ ወስ​ደ​ኸው እንደ ሆነ ሄጄ ወደ እኔ እን​ዳ​መ​ጣ​ውና ሽቱ እን​ድ​ቀ​ባው ወዴት እንደ አኖ​ር​ኸው ንገ​ረኝ” አለ​ችው።


ፈጥ​ናም ወደ ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስና ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ይወ​ደው ወደ ነበ​ረው ወደ​ዚያ ወደ ሌላዉ ደቀ መዝ​ሙር መጥታ፥ “ጌታ​ዬን ከመ​ቃ​ብር ወስ​ደ​ው​ታል፤ ወዴ​ትም እንደ ወሰ​ዱት አላ​ው​ቅም” አለ​ቻ​ቸው።


ጳው​ሎስ ግን መልሶ፥ “ለምን እን​ዲህ ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ? እያ​ለ​ቀ​ሳ​ችሁ ልቤን ትሰ​ብ​ሩ​ታ​ላ​ችሁ፤ እኔ እኮ ተስፋ የማ​ደ​ር​ገው መከ​ራ​ንና እግር ብረ​ትን ብቻ አይ​ደ​ለም፤ እኔ ግን በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለመ​ሞ​ትም ቢሆን የቈ​ረ​ጥሁ ነኝ” አለ።


ባልዋ ሕል​ቃ​ናም፥ “ሐና ሆይ!” አላት እር​ስ​ዋም፥ “ጌታዬ እነ​ሆኝ” አለ​ችው። እር​ሱም፥ “ለምን ታለ​ቅ​ሻ​ለሽ? ለም​ንስ አት​በ​ዪም? ለም​ንስ ልብሽ ያዝ​ን​ብ​ሻል? እኔስ ከዐ​ሥር ልጆች አል​ሻ​ል​ሽ​ምን?” አላት።