Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዮሐንስ 20:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አንቺ ሴት፥ ምን ያስ​ለ​ቅ​ስ​ሻል? ማን​ንስ ትሺ​ያ​ለሽ?” አላት፤ እር​ስዋ ግን የአ​ት​ክ​ልት ቦታ ጠባቂ መስ​ሎ​አት፥ “ጌታዬ፥ አንተ ወስ​ደ​ኸው እንደ ሆነ ሄጄ ወደ እኔ እን​ዳ​መ​ጣ​ውና ሽቱ እን​ድ​ቀ​ባው ወዴት እንደ አኖ​ር​ኸው ንገ​ረኝ” አለ​ችው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 እርሱም፣ “አንቺ ሴት፤ ለምን ታለቅሻለሽ? ማንንስ ትፈልጊአለሽ?” አላት። እርሷም የአትክልቱ ቦታ ጠባቂ መስሏት፣ “ጌታዬ፤ አንተ ወስደኸው ከሆነ፣ እባክህ እንድወስደው፣ የት እንዳኖርኸው ንገረኝ” አለችው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ኢየሱስም “አንቺ ሴት! ስለምን ታለቅሻለሽ? ማንንስ ትፈልጊያለሽ?” አላት። እርሷም የአትክልት ጠባቂ መስሎአት “ጌታ ሆይ! አንተ ወስደኸው እንደሆንህ ወዴት እንዳኖርኸው ንገረኝ፤ እኔም እወስደዋለሁ፤” አለችው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ኢየሱስ፥ “አንቺ ሴት ስለ ምን ታለቅሺአለሽ፤ ማንንስ ትፈልጊአለሽ?” አላት። እርስዋም አትክልተኛው መስሎአት፥ “ጌታ ሆይ! አንተ ወስደኸው እንደ ሆነ የት እንዳኖርከው እባክህ ንገረኝ፤ እኔ እወስደዋለሁ” አለችው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ኢየሱስም፦ “አንቺ ሴት፥ ስለ ምን ታለቅሻለሽ? ማንንስ ትፈልጊያለሽ?” አላት። እርስዋም የአትክልት ጠባቂ መስሎአት፦ “ጌታ ሆይ፥ አንተ ወስደኸው እንደ ሆንህ ወዴት እንዳኖርኸው ንገረኝ እኔም እወስደዋለሁ” አለችው።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 20:15
12 Referencias Cruzadas  

እነ​ዚያ መላ​እ​ክ​ትም፥ “አንቺ ሴት፥ ምን ያስ​ለ​ቅ​ስ​ሻል?” አሉ​አት፤ እር​ስ​ዋም፥ “ጌታ​ዬን ከመ​ቃ​ብር ውስጥ ወስ​ደ​ው​ታል፤ ወዴ​ትም እንደ ወሰ​ዱት አላ​ው​ቅም” አለ​ቻ​ቸው።


ከዚ​ህም በኋላ እን​ደ​ገና፥ “ማንን ትሻ​ላ​ችሁ?” ብሎ ጠየ​ቃ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “የና​ዝ​ሬ​ቱን ኢየ​ሱ​ስን” አሉት።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ዘወር ብሎ ሲከ​ተ​ሉት አየና፥ “ምን ትሻ​ላ​ችሁ?” አላ​ቸው።


እርሱ ግን “አትደንግጡ፤ የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ትፈልጋላችሁ፤ ተነሥቶአል፤ በዚህ የለም፤ እነሆ፥ እርሱን ያኖሩበት ስፍራ።


መልአኩም መልሶ ሴቶቹን አላቸው “እናንተስ አትፍሩ የተሰቀለውን ኢየሱስን እንድትሹ አውቃለሁና፤


እነ​ሣ​ለሁ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም እዞ​ራ​ለሁ፥ ነፍሴ የወ​ደ​ደ​ች​ውን በገ​በ​ያና በአ​ደ​ባ​ባይ እፈ​ል​ጋ​ለሁ፤ ፈለ​ግ​ሁት አላ​ገ​ኘ​ሁ​ትም። ጠራ​ሁት አል​መ​ለ​ሰ​ል​ኝም።


ኀዘ​ኔና ጭን​ቀቴ ስለ በዛ እስከ አሁን ድረስ እደ​ክ​ማ​ለ​ሁና ባር​ያ​ህን እንደ ኀጢ​አ​ተ​ኞች ሴቶች ልጆች አት​ቍ​ጠ​ራት።”


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም የሚ​ደ​ር​ስ​በ​ትን ሁሉ ዐውቆ ወደ እነ​ርሱ ወደ ውጭ ወጣና፥ “ማንን ትሻ​ላ​ችሁ?” አላ​ቸው።


ፈር​ተ​ውም ፊታ​ቸ​ውን ወደ ምድር አቀ​ረ​ቀሩ። እነ​ር​ሱም እን​ዲህ አሉ​አ​ቸው፥ “ሕያ​ዉን ከሙ​ታን ጋር ለምን ትሹ​ታ​ላ​ችሁ?


እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ክፉዎች ስትሆኑ መልካም ለመናገር እንዴት ትችላላችሁ? በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፍ ይናገራልና።


አንቺ በሴ​ቶች ዘንድ የተ​ዋ​ብሽ ሆይ፥ ከአ​ንቺ ጋር እን​ፈ​ል​ገው ዘንድ ልጅ ወን​ድ​ምሽ ወዴት ሄደ? ልጅ ወን​ድ​ም​ሽስ ወዴት ፈቀቅ አለ?


በመ​ን​ገ​ድም ከሰ​ዎች ጋር ያለ መስ​ሎ​አ​ቸው ነበር፤ ያንድ ቀን መን​ገ​ድ​ንም ከሄዱ በኋላ ዕለ​ቱን ከዘ​መ​ዶቹ፥ ከሚ​ያ​ው​ቁ​ትም ዘንድ ፈለ​ጉት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios