ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ፥ አሁንም አንተ አምላክ ነህ፤ ቃልህም እውነት ነው፤ ይህንም መልካም ነገር ለባሪያህ ተናግረሃል።
ዮሐንስ 17:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነውና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቃልህ እውነት ነው፤ በእውነትህ ቀድሳቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው። |
ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ፥ አሁንም አንተ አምላክ ነህ፤ ቃልህም እውነት ነው፤ ይህንም መልካም ነገር ለባሪያህ ተናግረሃል።
በመልካም ምድር የወደቀው ግን ቃሉን በበጎና በንጹሕ ልብ የሚሰሙና የሚጠብቁት፥ ታግሠውና ጨክነውም የሚያፈሩ ናቸው።
አሁንም በእግዚአብሔር ዘንድ የሰማሁትን እውነት የምነግራችሁን ሰው ልትገድሉኝ ትሻላችሁ፤ አብርሃምስ እንዲህ አላደረገም።
እኛስ ሁላችን ፊታችንን ገልጠን በመስተዋት እንደሚያይ የእግዚአብሔርን ክብር እናያለን፤ ከእግዚአብሔር መንፈስ እንደ ተሰጠን መጠን የእርሱን አርአያ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንገባለን።
እኛ ግን በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ! ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን ልናመሰግን ግድ አለብን፤ እግዚአብሔር በመንፈስ መቀደስ እውነትንም በማመን ለመዳን እንደ በኵራት መርጦአችኋልና፤