La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዮሐንስ 12:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ማር​ያም ግን ዋጋዉ የከ​በ​ረና የበዛ አንድ ነጥር የጥሩ ናር​ዶስ ሽቱ ወሰ​ደ​ችና የጌ​ታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን እግር ቀባ​ችው፤ በፀ​ጕ​ሯም አሸ​ችው፤ የዚያ ሽቱ መዓ​ዛም ቤቱን መላው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ማርያምም ዋጋው ውድ የሆነ፣ ግማሽ ሊትር ንጹሕ የናርዶስ ሽቱ አምጥታ የኢየሱስን እግሮች ቀባች፤ እግሮቹንም በጠጕሯ አበሰች፤ ቤቱንም የሽቱው መዐዛ ሞላው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ማርያምም ዋጋው እጅግ የከበረ የጥሩ ናርዶስ ሽቶ ንጥር ወስዳ የኢየሱስን እግሮች ቀባች፤ በጠጉርዋም አበሰቻችው፤ ቤቱም በሽቶው መዓዛ ተሞላ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚያን ጊዜ ማርያም ዋጋው እጅግ የከበረ ከንጹሕ ናርዶስ የተሠራ፥ ግማሽ ሊትር የሚሆን አንድ ብልቃጥ ሽቶ ወስዳ፥ የኢየሱስን እግሮች ቀባች፤ በጠጒርዋም አበሰቻቸው፤ ቤቱም በሽቶው መዓዛ ተሞላ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ማርያምም ዋጋው እጅግ የከበረ የጥሩ ናርዶስ ሽቱ ንጥር ወስዳ የኢየሱስን እግር ቀባች፤ በጠጕርዋም እግሩን አበሰች፤ ቤቱም ከናርዶስ ሽቱ ሞላ።

Ver Capítulo



ዮሐንስ 12:3
16 Referencias Cruzadas  

ከራሱ ጀምሮ እስከ ጢሙ፥ በል​ብሱ መደ​ረ​ቢያ ላይ፥ እስ​ከ​ሚ​ወ​ር​ደው እስከ አሮን ጢም ድረስ እን​ደ​ሚ​ፈስ ሽቱ ነው።


ንጉሡ በማ​ዕድ እስ​ከ​ሚ​ቀ​ርብ ድረስ፥ የእኔ ናር​ዶስ መዓ​ዛ​ውን ሰጠ።


የሽ​ቱሽ መዓዛ ከሽቱ ሁሉ መዓዛ ያማረ ነው፥ ስምህ እን​ደ​ሚ​ፈ​ስስ ሽቱ ነው፤ ስለ​ዚህ ደና​ግል ወደ​ዱህ።


እኅቴ ሙሽ​ሪት ሆይ፥ ጡቶ​ችሽ እን​ዴት ያማሩ ናቸው? ጡቶ​ችሽ ከወ​ይን ይልቅ እጅግ ያማሩ ናቸው። የሽ​ቱ​ሽም መዓ​ዛው ከሽቱ ሁሉ ይልቅ እጅግ ያማረ ነው።


ጥቂት ይበ​ቃል፤ ያም ባይ​ሆን አንድ ይበ​ቃል፤ ማር​ያ​ምስ የማ​ይ​ቀ​ሙ​አ​ትን መል​ካም ዕድል መረ​ጠች።”


አንተ ራሴን እንኳ ዘይት አል​ቀ​ባ​ኸ​ኝም፤ እር​ስዋ ግን እግ​ሬን ሽቱ ቀባ​ችኝ።


ማር​ያም ግን ጌታ​ች​ንን ሽቱ የቀ​ባ​ችው፥ እግ​ሩ​ንም በጠ​ጕ​ርዋ ያሸ​ችው ናት፤ ወን​ድ​ምዋ አል​ዓ​ዛ​ርም ታሞ ነበር።


ይህ​ንም ብላ ሄደች፤ እኅ​ቷን ማር​ያ​ም​ንም ቀስ ብላ ጠራ​ችና፥ “እነሆ፥ መም​ህ​ራ​ችን መጥቶ ይጠ​ራ​ሻል” አለ​ቻት።


ማር​ያ​ምም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ወደ አለ​በት ስፍራ ደረ​ሰ​ችና በአ​የ​ችው ጊዜ ከእ​ግሩ በታች ሰግዳ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ በዚህ ኑረህ ቢሆን ወን​ድሜ ባል​ሞ​ተም ነበር” አለ​ችው።


ቀድሞ በሌ​ሊት ወደ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ሄዶ የነ​በ​ረው ኒቆ​ዲ​ሞ​ስም መጣ፤ ቀብ​ተ​ውም የሚ​ቀ​ብ​ሩ​በ​ትን መቶ ወቄት የከ​ር​ቤና የሬት ቅል​ቅል ሽቶ አመጣ።