ዮሐንስ 12:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያ ቆመው ይሰሙ የነበሩ ሕዝብ ግን “ነጐድጓድ ነው” አሉ፤ “መልአክ ተናገረው” ያሉም አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ የነበሩት፣ ድምፁን የሰሙት አያሌ ሰዎች፣ “ነጐድጓድ ነው” አሉ፤ ሌሎች ደግሞ፣ “መልአክ ተናገረው” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያ ቆመው የነበሩትም ሕዝብ በሰሙ ጊዜ “ነጐድጓድ ነው፤” አሉ፤ ሌሎች “መልአክ ተናገረው፤” አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያ የቆሙ ሰዎች ይህን በሰሙ ጊዜ፥ “ነጐድጓድ ነው!” አሉ። ሌሎች ደግሞ “መልአክ ነው የተናገረው!” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያ ቆመው የነበሩትም ሕዝብ በሰሙ ጊዜ፦ “ነጐድጓድ ነው” አሉ፤ ሌሎች፦ “መልአክ ተናገረው” አሉ። |
እንዲህም ሆነ፤ በሦስተኛው ቀን በማለዳ ጊዜ ነጐድጓድና መብረቅ፥ ከባድም ደመና፥ ጉምም በሲና ተራራ ላይ ሆነ፤ እጅግም የበረታ የቀንደ መለከት ድምፅ ተሰማ፤ በሰፈሩም የነበሩት ሕዝብ ሁሉ ተንቀጠቀጡ።
ሕዝቡም ሁሉ ነጐድጓዱንና መብረቁን፥ የቀንደ መለከቱን ድምፅ፥ ተራራውንም ሲጤስ አዩ፤ ሕዝቡም ሁሉ ፈርተው ርቀው ቆሙ።
የኪሩቤልም የክንፎቻቸው ድምፅ ሁሉን የሚችል አምላክ እንደሚናገረው ያለ ድምፅ እስከ ውጭው አደባባይ ድረስ በሩቅ ይሰማ ነበር።
በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ፤ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ፤ መብረቅና ድምፅም ነጐድጓድም የምድርም መናወጥ ታላቅም በረዶ ሆነ።