ዮሐንስ 10:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “እኔ አማልክት ናችሁ አልሁ ተብሎ በኦሪታችሁ ተጽፎ የለምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “በሕጋችሁ፣ ‘እናንተ አማልክት ናችሁ አልሁ’ ተብሎ አልተጻፈምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፤ “እኔ ‘አማልክት ናችሁ አልሁ፤’ ተብሎ በሕጋችሁ ተጽፎ የለምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “በሕጋችሁስ ‘እናንተ አማልክት ናችሁ አልኩ’ የሚል ተጽፎ የለምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፦ “እኔ፦ ‘አማልክት ናችሁ አልሁ’ ተብሎ በሕጋችሁ የተጻፈ አይደለምን? |
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “እነሆ፥ እኔ ለፈርዖን አምላክ አድርጌሃለሁ፤ ወንድምህም አሮን ነቢይ ይሆንልሃል።
ሕዝቡም፥ “እኛስ ክርስቶስ ለዘለዓለም እንዲኖር በኦሪት ሰምተን ነበር፤ እንግዲህ እንዴት አንተ ‘የሰው ልጅ ከፍ ከፍ ይል ዘንድ አለው’ ትለናለህ? እንግዲህ ይህ የሰው ልጅ ማን ነው?” ብለው መለሱለት።
በኦሪትም፥ “ይህን ሕዝብ በሌሎች ቋንቋዎችና በሌላ አንደበት እናገራቸዋለሁ፤ እንዲሁም ሆኖ አይሰሙኝም ይላል እግዚአብሔር” ብሎአል።