ኢዩኤል 2:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ይሆናል፤ የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል፤ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ፥ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ይድናሉ። ደግሞም እግዚአብሔር የጠራቸው፥ የምሥራች የሚሰበክላቸው ይገኛሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ ሁሉ፣ ይድናል፤ እግዚአብሔርም እንዳለው፣ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም፣ መድኀኒት ይገኛል፤ ከትሩፋኑም መካከል እግዚአብሔር የጠራቸው በዚያ ይገኛሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም ይሆናል፥ የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል፥ ጌታም እንደ ተናገረ፥ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም የሚተርፉ ይኖራሉ። ደግሞም ጌታ የጠራቸው ይገኛሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔርንም ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል፤ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረው ከጽዮን ተራራና ከኢየሩሳሌም መዳን ይገኛል፤ ከሚድኑትም መካከል እግዚአብሔር የጠራቸው ይገኙበታል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ይሆናል፥ የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል፥ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ፥ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም መድኃኒት ይገኛል። ደግሞም እግዚአብሔር የጠራቸው፥ የምስራች የሚሰበከላቸው ይገኛሉ። |
በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ከአሦርና ከግብፅ፥ ከባቢሎንና ከኢትዮጵያ፥ ከኤላሜጤን፥ ከምሥራቅና ከምዕራብ ለቀሩት ለሕዝቡ ቅሬታ ይቀና ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ገና እጁን ይገልጣል።
በዚያም ቀን እግዚአብሔር ከእስራኤል የተረፉትን ያከብርና ከፍ ያደርግ ዘንድ በጌትነቱ ምክር በምድር ላይ ያበራል።
ጽድቄን አመጣኋት፤ ከእኔ ዘንድ የምትገኝ መድኀኒትንም አላዘገይም፤ ከጽዮን ለክብር እንዲሆን መድኀኒትን ለእስራኤል ሰጥቻለሁ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፥ “የያዕቆብ ቤት ሆይ! ደስ ይበላችሁ፤ በአሕዛብም አለቆች ላይ እልል በሉ፤ አውሩ፤ አመስግኑም፤ እግዚአብሔርም ሕዝቡን የእስራኤልን ቅሬታ አድኖአል በሉ።
እነሆ የጌታ የእግዚአብሔር ዐይኖች በኀጢአተኛ መንግሥት ላይ ናቸው፤ ከምድርም ፊት አጠፋታለሁ፤ ነገር ግን የያዕቆብን ቤት ፈጽሜ አላጠፋም፤ ይላል እግዚአብሔር።
“ነገር ግን በጽዮን ተራራ ላይ መድኀኒት ይሆናል፤ እርሱም ቅዱስ ይሆናል፤ የያዕቆብም ቤት ሰዎች የወረሱአቸውን ይወርሳሉ።
ሦስተኛውንም ክፍል ወደ እሳት አገባለሁ፥ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፥ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፣ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፣ እኔም፦ ይህ ሕዝቤ ነው እላለሁ፣ እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላኬ ነው ይላል።
ከዚህ ቦታ ያይደሉ ሌሎች በጎችም አሉኝ፤ እነርሱንም ወደዚህ አመጣቸው ዘንድ ይገባኛል፤ ቃሌንም ይሰሙኛል፤ ለአንድ እረኛም አንድ መንጋ ይሆናሉ።
የቀሩት ሰዎችና ስሜም የተጠራባቸው አሕዛብ ሁሉ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ፥ ይላል ይህን የሚያደርግ እግዚአብሔር፤
ከዚህ በኋላም መላው እስራኤል ይድናሉ፤ መጽሐፍ እንዲህ እንዳለ፥ “አዳኝ ከጽዮን ይወጣል፤ ከያዕቆብም ኀጢአትን ያስወግዳል።
ኢሳይያስም ድምፁን ከፍ አድርጎ ስለ እስራኤል እንዲህ አለ፥ “የእስራኤል ልጆች ቍጥራቸው እንደ ባሕር አሸዋ ቢሆንም የተረፉት ይድናሉ።
በቆሮንቶስ ሀገር ላለች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ለከበሩና ቅዱሳን ለተባሉ የእነርሱና የእኛ ጌታ የሆነውን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በየስፍራው ለሚጠሩ ሁሉ፥
እናንተ ግን፥ የሕያው እግዚአብሔር ከተማ ወደምትሆን ወደ ጽዮን ተራራ፥ በሰማያት ወደ አለችው ኢየሩሳሌም፥ ደስ ብሎአቸው ወደሚኖሩ አእላፍ መላእክትም ደርሳችኋል።