ኢዩኤል 2:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በላይ በሰማይ ድንቆችን አሳያለሁ፤ በታች በምድርም ደምና እሳት የጢስም ጭጋግ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ድንቆችን በሰማያት፣ እንዲሁም በምድር፣ ደምና እሳት፣ የጢስም ዐምድ አሳያለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በላይ በሰማይ ድንቆችን አሳያለሁ፥ በታች በምድርም ደምና እሳት የጢስም ጭጋግ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በሰማይና በምድር፥ ድንቅ ነገሮችን አሳያለሁ፤ ደምና እሳት፥ የጢስ ዐምድም ይታያል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በላይ በሰማይ ድንቆችን አሳያለሁ፥ በታች በምድርም ደምና እሳት የጢስም ጭጋግ። |
መዓዛዋ እንደ ከርቤና እንደ ዕጣን የሆነው፥ ከልዩ የሽቱ ቅመም ሁሉ የሆነው፥ ይህች ከምድረ በዳ እንደ ጢስ ዐምድ የወጣችው ማን ናት?
ስለዚህ ምድር ታለቅሳለች፤ በላይም ሰማይ ይጠቍራል፤ ተናግሬአለሁና፤ አልጸጸትም ወደፊት እሮጣለሁ፤ ከእርስዋም አልመለስም።
የጋይም ሰዎች ወደ ኋላቸው ዞረው በተመለከቱ ጊዜ የከተማዪቱ ጢስ ወደ ሰማይ ሲወጣ አዩ፤ ወዲህና ወዲያ መሸሽ አልቻሉም፤ ወደ ምድረ በዳም የሸሹ ሕዝብ በሚያሳድዱአቸው ላይ ተመለሱ።
ፊተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ ደምም የተቀላቀለበት በረዶና እሳት ሆነ፤ ወደ ምድርም ተጣለ፤ የምድርም ሲሶው ተቃጠለ፤ የዛፎችም ሲሶው ተቃጠለ፤ የለመለመም ሣር ሁሉ ተቃጠለ።
የተደበቁትም ሰዎች ከከተማው ብዙ ጢስ እንደ ደመና እንዲያስነሡ በእስራኤል ልጆችና በተደበቁት ሰዎች መካከል ምልክት ተደርጎ ነበር።
ምልክቱም በጢሱ ዐምድ ከከተማው ሊወጣ በጀመረ ጊዜ ብንያማውያን ወደኋላቸው ተመለከቱ፤ እነሆም፥ የሞላ ከተማው ጥፋት ወደ ሰማይ ወጣ።