ኢዩኤል 1:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈሳሹ ውኃ ደርቆአልና፥ እሳቱም የምድረ በዳውን ውበት በልቶአልና የምድር አራዊት ወደ አንተ አንጋጠጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዱር አራዊት እንኳ ወደ አንተ አለኸለኹ፤ ወራጁ ውሃ ደርቋል፤ ያልተነካውንም መሰማሪያ እሳት በልቶታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈሳሹ ውኃ ደርቆአልና፥ እሳቱም የምድረ በዳውን ማሰማርያ በልቶአልና የምድር አራዊት ወደ አንተ አለኸለኹ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንዞች ስለ ደረቁባቸው፥ የሜዳውም ሣር ሁሉ ስለ ተቃጠለባቸው፥ የዱር አራዊት እንኳ ወደ አንተ ይጮኻሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈሳሹ ውኃ ደርቆአልና፥ እሳቱም የምድረ በዳውን ማሰማርያ በልቶአልና የምድር አራዊት ወደ አንተ አለኸለኹ። |
አክዓብም አብድዩን፥ “በሀገሩ መካከል ወደ ውኃ ምንጭ ሁሉና ወደ ፈፋ ሁሉ ና እንሂድ፤ እንስሶችም ሁሉ እንዳይጠፉ ፈረሶችንና በቅሎችን የምናድንበት ሣር ምናልባት እናገኝ እንደ ሆነ” አለው።
ከጥንት ከእኔና ከአንተ በፊት የነበሩ ነቢያት በብዙ ሀገርና በታላላቅ መንግሥታት ላይ ስለ ሰልፍና ስለ ክፉ ነገር ስለ ቸነፈርም ትንቢት ተናገሩ።
እንግዲህ ለራሳችን ምን እንሰብስብ? የእንስሳት ጠባቂዎች አለቀሱ፤ ማሰማሪያ የላቸውምና፥ የበጎች መንጋዎችም ጠፍተዋልና።