ኢዩኤል 1:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ! እሳት የምድረ በዳውን ውበት አጥፍቶአልና፥ ነበልባሉም የዱሩን ዛፍ ሁሉ አቃጥሎአልና ወደ አንተ እጮኻለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ እጣራለሁ፤ ያልተነካውን መሰማሪያ እሳት በልቶታልና፤ የዱሩን ዛፍ ሁሉ ነበልባል አቃጥሎታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ እሳት የምድረ በዳውን ማሰማርያ በልቶአልና፥ ነበልባሉም የዱሩን ዛፍ ሁሉ አቃጥሎአልና ወደ አንተ እጮኻለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! የሜዳውን ሣር ሁሉ እሳት ስለ በላው፥ የዱሩንም ዛፍ እሳት ስለ አቃጠለው እኔ ወደ አንተ እጮኻለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤቱ፥ እሳት የምድረ በዳውን ማሰማርያ በልቶአልና፥ ነበልባሉም የዱሩን ዛፍ ሁሉ አቃጥሎአልና ወደ አንተ እጮኻለሁ። |
በተራሮቹ ላይ አልቅሱ፤ በምድረ በዳም ጎዳና ላይ እዘኑ፤ ሰው ጠፍትዋልና፤ የሚመላለስም የለምና ሙሾውንም አሙሹ፤ የሰማይ ወፍ ድምፅንም እስከ ከብት ድምፅ ድረስ አይሰሙም፤ ደንግጠውም ተማርከው ሄዱ።
በውኑ ስለዚህ ነገር በመቅሠፍት አልጐበኝምን? ይላል እግዚአብሔር፤ ነፍሴስ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አትበቀልምን?
እሳት በፊታቸው ትበላለች፥ በኋላቸውም ነበልባል ታቃጥላለች፤ ምድሪቱ በፊታቸው እንደ ደስታ ገነት፥ በኋላቸውም እንደ ምድረ በዳ በረሃ ናት፤ ከእርሱም የሚያመልጥ የለም።
እንዲህም አለ፥ “እግዚአብሔር ከጽዮን ሆኖ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይናገራል፤ ከኢየሩሳሌምም ሆኖ ቃሉን ይሰጣል፤ የእረኞችም ማሰማሪያዎች ያለቅሳሉ፤ የቀርሜሎስም ራስ ይደርቃል።”
ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ አሳየኝ፤ እነሆም ጌታ እግዚአብሔር ለመፍረድ በቃሉ እሳትን ጠራ፤ እርስዋም ታላቁን ቀላይና ምድርን በላች።
እንግዲህ እግዚአብሔር በመዓልትና በሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ለወዳጆቹ አይፈርድምን? ወይስ ቸል ይላቸዋልን?