ኢዮብ 8:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቅኖችን አፍ ሳቅ ይሞላል፥ ከንፈሮቻቸውንም ምስጋና ይሞላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ ገና አፍህን በሣቅ፣ ከንፈሮችህንም በእልልታ ይሞላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አፍህን እንደገና በሳቅ፥ ከንፈሮችህንም በእልልታ ይሞላዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ አንተንም በደስታ እንድትስቅና ‘እልል’ እንድትል ያደርግሃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አፍህን እንደ ገና ሳቅ ይሞላል፥ ከንፈሮችህንም እልልታ ይሞላል። |
እግዚአብሔርም በታላቅ ደስታ ደስ አሰኝቶአቸዋልና በዚያ ቀን ትልቅ መሥዋዕት አቀረቡ፤ ደስም አላቸው፤ ሴቶቹና ልጆቹም ደግሞ ደስ አላቸው፤ ደስታቸውም በኢየሩሳሌም ከሩቅ ተሰማ።
እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፥ ቤትን የሚሠሩ በከንቱ ይደክማሉ፤ እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፥ የሚጠብቁ በከንቱ ይተጋሉ።
በማለዳ መገሥገሣችሁም ከንቱ ነው። ለወዳጆቹ እንቅልፍን በሰጠ ጊዜ፥ እናንተ የመከራን እንጀራ የምትበሉ፥ ከተቀመጣችሁበት ተነሡ።