Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዮብ 8:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ስለዚህ አንተንም በደስታ እንድትስቅና ‘እልል’ እንድትል ያደርግሃል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 እንደ ገና አፍህን በሣቅ፣ ከንፈሮችህንም በእልልታ ይሞላል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 አፍህን እንደገና በሳቅ፥ ከንፈሮችህንም በእልልታ ይሞላዋል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 የቅ​ኖ​ችን አፍ ሳቅ ይሞ​ላል፥ ከን​ፈ​ሮ​ቻ​ቸ​ው​ንም ምስ​ጋና ይሞ​ላል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 አፍህን እንደ ገና ሳቅ ይሞላል፥ ከንፈሮችህንም እልልታ ይሞላል።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 8:21
13 Referencias Cruzadas  

ሣራ “እግዚአብሔር ደስታና ሳቅ አመጣልኝ፤ ስለዚህ ይህን ነገር የሚሰማ ሁሉ ከእኔ ጋር ይስቃል” አለች።


በዚያም ዕለት ብዙ መሥዋዕት ቀረበ፤ ሕዝቡም እግዚአብሔር ደስ ስላሰኛቸው ታላቅ ሐሴት አደረጉ፤ ሴቶችም፥ ልጆችም አብረው ተደስተዋል፤ በኢየሩሳሌም የነበረው የእልልታቸው ድምፅ እስከ ሩቅ ድረስ ይሰማ ነበር።


ነገር ግን ከእነርሱ አንዳቸው እንኳ በሌሊት ጥበቃ የሚያደርገው ፈጣሪ አምላክ ወዴት ነው ብሎ አይጠይቅም።


የኀያላን አጥቂነትና ራብ አያስደነግጡህም፤ የምድርንም አራዊት አትፈራም።


በምድር ላይ የምትኖሩ ሕዝቦች ሁሉ ለእግዚአብሔር “እልል!” በሉ!


እግዚአብሔር ወደ ኢየሩሳሌም መልሶ ባመጣን ጊዜ ሕልም እንጂ እውነት አልመሰለንም ነበር።


አፋችን በሳቅ ተሞላ፤ አንደበታችንም የደስታ መዝሙር ዘመረ፤ በዚህም ምክንያት አሕዛብ፦ “እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገላቸው” አሉን።


ዘሩን ተሸክመው ሲሄዱ ያለቅሱ የነበሩት፥ በደስታ እየዘመሩ ነዶአቸውን ተሸክመው ይመለሳሉ።


ጻድቃን ሆይ! በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ሐሴትም አድርጉ፤ ልበ ቅኖች ሆይ! እልል በሉ!


በምድር ላይ የምትኖሩ ሕዝቦች ሁሉ ለእግዚአብሔር በደስታ ዘምሩ! በመዝሙርና በእልልታ አመስግኑት!


እናንተ አሁን የምትራቡ፥ በኋላ ትጠግባላችሁና የተባረካችሁ ናችሁ! እናንተ አሁን የምታለቅሱ፥ በኋላ ትስቃላችሁና የተባረካችሁ ናችሁ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos