ኢዮብ 6:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምግብ ያለ ጨው ይበላልን? የጎመን ዘር ጭማቂስ ይጣፍጣልን? ወይስ ለከንቱ ጣዕም አለውን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም የማይጣፍጥ ምግብ ያለ ጨው ይበላልን? ወይስ የዕንቍላል ውሃ ጣዕም አለውን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የማይጣፍጥስ ነገር ያለ ጨው ይበላልን? ወይስ የእንቁላል ውኃ ይጥማልን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጨው ያልገባበት ጣዕም ያጣ ምግብ ይበላልን? የእንቊላልስ ውሃ ይጣፍጣልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የማይጣፍጥስ ነገር ያለ ጨው ይበላልን? ወይስ የእንቍላል ውኃ ይጥማልን? |
በውኑ የሜዳ አህያ ሣር እያለው በከንቱ ይጮኻልን? የሚበላውን ፈልጎ አይደለምን? ወይስ በሬ በበረት ውስጥ ገለባ ሳለው ይጮኻልን?
የምታቀርቡት ቍርባን ሁሉ በጨው ይጣፈጣል፤ የአምላክህም ቃል ኪዳን ጨው ከቍርባንህ አይጕደል፤ በቍርባናችሁ ሁሉ ላይ ጨው ትጨምራላችሁ።