Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዮብ 6:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የማይጣፍጥስ ነገር ያለ ጨው ይበላልን? ወይስ የእንቁላል ውኃ ይጥማልን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 የማይጣፍጥ ምግብ ያለ ጨው ይበላልን? ወይስ የዕንቍላል ውሃ ጣዕም አለውን?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ጨው ያልገባበት ጣዕም ያጣ ምግብ ይበላልን? የእንቊላልስ ውሃ ይጣፍጣልን?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ምግብ ያለ ጨው ይበ​ላ​ልን? የጎ​መን ዘር ጭማ​ቂስ ይጣ​ፍ​ጣ​ልን? ወይስ ለከ​ንቱ ጣዕም አለ​ውን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 የማይጣፍጥስ ነገር ያለ ጨው ይበላልን? ወይስ የእንቍላል ውኃ ይጥማልን?

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 6:6
13 Referencias Cruzadas  

ለእያንዳንዱ እንዴት መልስ መስጠት እንደሚገባችሁ እንድታውቁ ንግግራችሁ ሁልጊዜ፥ በጨው እንደ ተቀመመ፥ በጸጋ ይሁን።


የምታቀርበውን የእህል ቁርባን ሁሉ በጨው ታጣፍጠዋለህ፤ የአምላክህንም የቃል ኪዳን ጨው ከእህል ቁርባንህ እንዳታጐድል፤ በቁርባንህ ሁሉ ላይ ጨው ታቀርባለህ።


“ጨው መልካም ነው፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፍጣል?


ቃልህ ለጉሮሮዬ ጣፋጭ ነው፥ ከማርና ከወለላ ይልቅ ለአፌ ጣፈጠኝ።


ምላስ መብልን እንደሚያጣጥም፥ ጆሮም ቃላትን ይለያልና።


“እንደዚህ ያለ ነገር አብዝቼ ሰማሁ፥ እናንተ ሁላችሁ የምታደክሙ አጽናኞች ናችሁ።


ምላስ የምግብን ጣዕም እንደሚለይ፥ ጆሮም የቃላትን እውነት ይለይ የለምን?


በውኑ በአንደበቴ በደል ይገኛልን? ምላሴ የተንኰልን ቃና መለየት አይችልምን?”


የቅንነት ቃል እንዴት ኃይለኛ ነው! የእናንተ ሙግት ግን ምን ይገሥጻል?


እናንተ የምድሪቱ ጨው ናችሁ፤ ጨው ጣዕሙን ቢያጣ ግን በምን ይጣፍጣል? በሰው ለመረገጥ ወደ ውጭ ከመጣል በስተቀር ወደ ፊት ለምንም አይጠቅምም።


በውኑ የሜዳ አህያ ሣር እያለው ይጮኻልን? ወይስ በሬ ገለባ እያለው ይጮኻልን?


ሰውነቴ ትነካው ዘንድ እንቢ አለችው፥ እንደሚያስጸይፍ መብል ሆነብኝ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios