La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢዮብ 42:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

መስ​ማ​ት​ንስ ስለ አንተ ቀድሞ በጆ​ሮዬ ሰምቼ ነበር፤ አሁን ግን ዐይኔ አየ​ችህ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ጆሮዬ ስለ አንተ ሰምታ ነበር፤ አሁን ግን ዐይኔ አየችህ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

መስማትንስ በጆሮ በመስማት ሰምቼ ነበር፥ አሁን ግን ዓይኔ አየችህ፥

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እኔ እስከ አሁን ስለ አንተ የማውቀው፥ ሰዎች የነገሩኝን በመስማት ብቻ ነበር፤ አሁን ግን በዐይኖቼ አየሁህ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

መስማትንስ በጆሮ በመስማት ሰምቼ ነበር፥ አሁን ግን ዓይኔ አየችህ፥

Ver Capítulo



ኢዮብ 42:5
16 Referencias Cruzadas  

እነሆ ይህ የመ​ን​ገዱ ክፍል ነው፤ የቀ​ሩ​ት​ንም ነገ​ሮ​ቹን እን​ሰ​ማ​ለን፤ በሚ​ያ​ደ​ር​ግ​በ​ትስ ጊዜ የነ​ጐ​ድ​ጓ​ዱን ኀይል የሚ​ያ​ውቅ ማን ነው?”


ሞትና ሲኦል ወሬ​ዋን በጆ​ሮ​ቻ​ችን ሰማን ብለ​ዋል።


በዚ​ያን ጊዜ የሰ​ዎ​ችን ማስ​ተ​ዋል ይከ​ፍ​ታል፥ ግርማ ባለው ራእ​ይም ያስ​ደ​ነ​ግ​ጣ​ቸ​ዋል፤


ነገር ግን አንተ አን​ዳች እው​ነት አድ​ር​ገህ ቢሆን ኖሮ፥ ይህ ሁሉ ባል​ደ​ረ​ሰ​ብ​ህም ነበር። በእኔ ዘንድ ነገር ይነ​ሣል፤ ዦሮ​ዬም ከእ​ርሱ ድም​ፅን ትሰ​ማ​ለች፤ ጥን​ቱን የነ​ገ​ረ​ኝን አላ​ም​ነ​ው​ምን?


ስለ​ዚህ ራሴን እን​ቃ​ለሁ፤ ሰው​ነ​ቴም ቀለጠ። እኔ አፈ​ርና አመድ እንደ ሆንሁ አው​ቃ​ለሁ።”


ከዚ​ህም በኋላ ንጉሡ ዖዝ​ያን በሞ​ተ​በት ዓመት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በረ​ዥ​ምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀ​ምጦ አየ​ሁት፤ ምስ​ጋ​ና​ውም ቤቱን ሞል​ቶት ነበር።


እኔም፥ “ከን​ፈ​ሮች የረ​ከ​ሱ​ብኝ ሰው በመ​ሆኔ፥ ከን​ፈ​ሮ​ቻ​ቸው በረ​ከ​ሱ​ባ​ቸው ሕዝብ መካ​ከል በመ​ቀ​መጤ ዐይ​ኖች የሠ​ራ​ዊ​ትን ጌታ ንጉ​ሡን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ አዩ ጠፍ​ቻ​ለ​ሁና ወዮ​ልኝ!” አልሁ።


አቤቱ፥ ዝናህን ሰምቼ ፈራሁ፣ አቤቱ፥ በዓመታት መካከል ሥራህን ፈጽም፣ በዓመታት መካከል ትታወቅ፣ በመዓት ጊዜ ምሕረትን አስብ።


በአ​ባቱ ዕቅፍ ያለ አንድ ልጅ እርሱ ገለ​ጠ​ልን እንጂ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንስ ከቶ ያየው የለም።


ኢሳ​ይ​ያስ ጌት​ነ​ቱን አይ​ቶ​አ​ልና፥ ይህን ተና​ገረ፤ ስለ እር​ሱም መሰ​ከረ።


እኔን ያየ የላ​ከ​ኝን አየ።


ማመን ከመ​ስ​ማት ነው፤ መስ​ማ​ትም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ነው።