ኢዮብ 26:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 እነሆ ይህ የመንገዱ ክፍል ነው፤ የቀሩትንም ነገሮቹን እንሰማለን፤ በሚያደርግበትስ ጊዜ የነጐድጓዱን ኀይል የሚያውቅ ማን ነው?” Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 እነዚህ የሥራው ዳር ዳር ናቸው፤ ስለ እርሱ የሰማነው ምንኛ አነስተኛ ነው! የኀይሉንስ ነጐድጓድ ማን ሊያስተውል ይችላል?” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 እነሆ፥ እነኚህ የሥራዎቹ ጫፎች ብቻ ነው፥ ይህም የሰማነው ነገር ምንኛ ጥቂት ነው! የኃይሉንስ ነጐድጓድ ማን ማስተዋል ይችላል?” Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 እነዚህ ሁሉ እግዚአብሔር ከሚሠራቸው ነገሮች ጥቂቶቹ ናቸው፤ የምንሰማውም ሹክሹክታውን ብቻ ነው፤ የኀይሉን ነጐድጓድማ ማን ሊያስተውል ይችላል?” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 እነሆ፥ ይህ የመንገዱ ዳርቻ ብቻ ነው፥ ይህም የሰማነው ነገር ምንኛ ጥቂት ነው! የኃይሉንስ ነጐድጓድ ያስተውል ዘንድ ማን ይችላል? Ver Capítulo |
እግዚአብሔር ጠላቶቹን ያደክማቸዋል፤ እግዚአብሔር ብቻ ቅዱስ ነው፤ ጥበበኛ በጥበቡ አይመካ፤ ኀይለኛም በኀይሉ አይመካ፤ ሀብታምም በሀብቱ አይመካ፤ የሚመካ ግን በዚህ ይመካ፤ እግዚአብሔርን በማወቅና በማስተዋል፤ በምድርም መካከል ፍርድንና እውነትን በማድረግ፥ እግዚአብሔር ወደ ሰማይ ወጣ፤ አንጐደጐደም። ጻድቅ እርሱ እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል፤ ለንጉሦቻችንም ኀይልን ይሰጣል፤ የመሲሑንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል።”