ኢዮብ 4:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መንፈሴም በፊቴ ዐለፈ፥ ሥጋዬም፥ ጠጕሬም ተቈጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መንፈስ ሽው ብሎ በፊቴ ዐለፈ፤ የገላዬም ጠጕር ቆመ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መንፈስም በፊቴ አለፈ፥ የሥጋዬ ጠጉር ቆመ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የነፋስ ሽውታ በፊቴ ላይ አለፈ፤ ከድንጋጤ የተነሣ ጠጒሬ ተንጨፍርሮ ቆመ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መንፈስም በፊቴ አለፈ፥ የሥጋዬ ጠጕር ቆመ። |
ተነሣሁ፤ ነገር ግን አላወቅሁም፥ ተመለከትሁ፥ በዐይኖቼም ፊት መልክ አልነበረም። ነገር ግን ጥላን አያለሁ፤ ድምፅንም እሰማለሁ፦
ሽማግሎች ይደነግጣሉ፤ እንደምትወልድ ሴትም ምጥ ይይዛቸዋል፤ እርስ በርሳቸውም ይገዳደላሉ፤ ይደነቃሉ፤ ፊታቸውም እንደ እሳት ይንበለበላል።
መላእክት ሁሉ መናፍስት አይደሉምን? የዘለዓለም ሕይወትን ይወርሱ ዘንድ ስለ አላቸው ሰዎችስ ለአገልግሎት ይላኩ የለምን?