እግዚአብሔርም አለ፥ “ሰውን በአርኣያችንና በአምሳላችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሣዎችንና የምድር አራዊትን፥ የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድርም ላይ የሚንቀሳቀሱትን ሁሉ ይግዛ።”
ኢዮብ 39:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጕልበቱስ ብርቱ ስለሆነ ትታመነዋለህን? ተግባርህንስ ለእርሱ ትተዋለህን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጕልበቱ ብርቱ ስለ ሆነ ትተማመንበታለህ? ከባዱን ሥራህንስ ለርሱ ትተዋለህ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጉልበቱስ ብርቱ ስለ ሆነ በእርሱ ትታመናለህን? አድካሚ ሥራህን ለእርሱ ትተዋለህን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለ ብርቱ ጥንካሬው በእርሱ ትተማመናለህን? ከባድ ሥራህንስ ለእሱ ትተውለታለህን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጕልበቱስ ብርቱ ስለ ሆነ ትታመነዋለህን? ተግባርህንስ ለእርሱ ትተዋለህን? |
እግዚአብሔርም አለ፥ “ሰውን በአርኣያችንና በአምሳላችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሣዎችንና የምድር አራዊትን፥ የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድርም ላይ የሚንቀሳቀሱትን ሁሉ ይግዛ።”
እግዚአብሔርም ባረካቸው፤ እንዲህም አላቸው፥ “ብዙ፤ ተባዙ፤ ምድርንም ሙሉአት፤ ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሣዎችንና የምድር አራዊትን፥ የሰማይ ወፎችንና እንስሳትንም ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው።”
አስፈሪነታችሁና አስደንጋጭነታችሁ በምድር አራዊት፥ በሰማይ ወፎች፥ በምድር ላይ በሚንቀሳቀሱትም፥ በባሕር ዓሦችም ሁሉ ላይ ይሁን፤ እነርሱንም በእጃችሁ ሰጠኋችሁ።
እግዚአብሔር በቃሉ ሁሉ የታመነ ነው፥ በሥራውም ሁሉ ጻድቅ ነው፤ እግዚአብሔር የተፍገመገሙትን ሁሉ ይደግፋቸዋል፥ እግዚአብሔር የወደቁትን ያነሣቸዋል።
ነገር ግን፥ በፈረስ ላይ ተቀምጠን እንሸሻለን እንጂ እንዲህ አይሆንም አላችሁ፤ ስለዚህም ትሸሻላችሁ፤ ደግሞም በፈጣን ፈረስ ላይ እንቀመጣለን አላችሁ፤ ስለዚህም የሚያሳድዱአችሁ ፈጣኖች ይሆናሉ።
ተባትና እንስት አንበሳ፥ እፉኝትም፥ ነዘር እባብም፥ በሚወጡባት በመከራና በጭንቀት ምድር በኩል ብልጽግናቸውን በአህዮች ጫንቃ ላይ፥ መዛግብቶቻቸውንም በግመሎች ሻኛ ላይ እየጫኑ ወደማይጠቅሙአቸው ሕዝብ ይሄዳሉ።
ቤል ወደቀ፤ ዳጎን ተሰባበረ፤ ምስሎቻቸውም እንደ ትቢያ ሆኑ፤ አራዊትና እንስሳም ይረግጡአቸዋል፤ እንደ ፋንድያም ሸክም የሚያጸይፉ ናቸውና አያነሡአቸውም።