“በመቃብር ውስጥ ምነው በጠበቅኸኝ ኖሮ! ቍጣህ እስኪበርድም ድረስ በሸሸግኸኝ ኖሮ! እስከምታስበኝም ምነው ቀጠሮ በሰጠኸኝ ኖሮ!
ኢዮብ 3:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኃጥኣን በዚያ በቍጣው መቅሠፍት ይቃጠላሉ፤ በዚያም በሥጋቸው የተጨነቁት ያርፋሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ክፉዎች ማወካቸውን ይተዋሉ፤ ደካሞችም በዚያ ያርፋሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉዎች በዚያ መናደዳቸውን ይተዋሉ፥ በዚያም ደካሞች ያርፋሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያ ክፉዎች አስቸጋሪነታቸው ይቀራል፤ በአድካሚ ሥራም የኖሩ ያርፋሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ክፉዎች በዚያ መናደዳቸውን ይተዋሉ፥ በዚያም ደካሞች ያርፋሉ። |
“በመቃብር ውስጥ ምነው በጠበቅኸኝ ኖሮ! ቍጣህ እስኪበርድም ድረስ በሸሸግኸኝ ኖሮ! እስከምታስበኝም ምነው ቀጠሮ በሰጠኸኝ ኖሮ!
ፍቅራቸውና ጥላቸው ቅንአታቸውም በአንድነት እነሆ፥ ጠፍቶአል፤ ከፀሓይ በታችም በሚሠራው ነገር ሁሉ ለዘለዓለም ዕድል ፈንታ ከእንግዲህ ወዲህ የላቸውም።
ለእናንተ ለወዳጆች እላችኋለሁ፦ ሥጋችሁን የሚገድሉትን አትፍሩአቸው፤ ከዚህም የበለጠ ማድረግ የሚችሉት የላቸውም።
ከሰማይም እንዲህ የሚል ድምፅ ሰማሁ። “ይህንን ጻፍ፡ ከእንግዲህ ወዲህ በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብፁዓን ናቸው።” መንፈስም “አዎን! ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ፥ ሥራቸውም ይከተላቸዋል፤” ይላል።
እግዚአብሔርም እስራኤልን ከአንተ ጋር በፍልስጥኤማውያን እጅ አሳልፎ ይሰጣል፤ ነገም አንተና ከአንተ ጋር ያሉ ልጆችህ ትወድቃላችሁ፥ እግዚአብሔርም የእስራኤልን ጭፍራ ደግሞ በፍልስጥኤማውያን እጅ አሳልፎ ይሰጣል።