Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 3:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ክፉዎች በዚያ መናደዳቸውን ይተዋሉ፥ በዚያም ደካሞች ያርፋሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 በዚያ ክፉዎች ማወካቸውን ይተዋሉ፤ ደካሞችም በዚያ ያርፋሉ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 በዚያ ክፉዎች አስቸጋሪነታቸው ይቀራል፤ በአድካሚ ሥራም የኖሩ ያርፋሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ኃጥ​ኣን በዚያ በቍ​ጣው መቅ​ሠ​ፍት ይቃ​ጠ​ላሉ፤ በዚ​ያም በሥ​ጋ​ቸው የተ​ጨ​ነ​ቁት ያር​ፋሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ክፉዎች በዚያ መናደዳቸውን ይተዋሉ፥ በዚያም ደካሞች ያርፋሉ።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 3:17
16 Referencias Cruzadas  

በሲኦል ውስጥ ምነው በሰወርኸኝ ኖሮ! ቁጣህ እስኪያልፍ ድረስ በሸሸግኸኝ ኖሮ! ቀጠሮም አድርገህ ምነው ባሰብኸኝ ኖሮ!


ወደ ሲኦል ይወርዳልን? አብረን ወደ አፍር ውስጥ እንገባ የለምን?”


ወይም እንደ ተደበቀበ ጭንጋፍ፥ ብርሃንም እንዳላዩ ሕፃናት በሆንሁ ነበር።


በዚያ ግዞተኞች በአንድነት ተዘልለው ተቀምጠዋል፥ የአስጨናቂውን ድምፅ አይሰሙም።


እኔም እስከ ዛሬ በሕይወት ካሉት ይልቅ በቀድሞ ዘመን የሞቱትን አመሰገንሁ፥


ፍቅራቸውና ጥላቸው ቅንዓታቸውም በአንድነት ከወዲሁ ጠፍቶአል፥ ከፀሐይ በታችም በሚሠራው ነገር ለዘለዓለም እድል ፈንታ ከእንግዲህ ወዲህ የላቸውም።


ሥጋን የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይችሉትን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንና ሥጋን በገሃነም ሊያጠፋ የሚችለውን እርሱን ፍሩ።


ለእናንተም ለወዳጆቼ እንዲህ እላችኋለሁ፤ ሥጋን የሚገድሉትን፥ ከዚያ አልፈው ግን ፈጽሞ ምንም ማድረግ የማይችሉትን አትፍሩ።


እንግዲህ እንደዚያ እንደ አለመታዘዝ ምሳሌ ማንም እንዳይወድቅ ወደዚያ ዕረፍት ለመግባት እንትጋ።


እንግዲያስ የሰንበት ዕረፍት ለእግዚአብሔር ሕዝብ ቀርቶላቸዋል።


ያ ጻድቅ ሰው፥ በመካከላቸው ሲኖር ዕለት ከዕለት የዐመፀኞችን ሴሰኛ ኑሮ እያየና እየሰማ በክፉ ሥራቸው ጻድቅ ነፍሱን ቢያስጨንቅም፤


ከሰማይም እንዲህ የሚል ድምፅ ሰማሁ። “ይህንን ጻፍ፥ ከእንግዲህ ወዲህ በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብፁዓን ናቸው።” መንፈስም “አዎን! ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ፥ ሥራቸው ይከተላቸዋልና፤” ይላል።


ገና ጌታ አንተንና እስራኤልን ለፍልስጥኤማውያን አሳልፎ ይሰጣል፤ አንተና ልጆችህም ነገ ከእኔ ጋር ትሆናላችሁ፤ እንዲሁም እግዚአብሔር የእስራኤልን ሠራዊት ለፍልስጥኤማውያን አሳልፎ ይሰጣል።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos