ኢዮብ 25:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ጥንቱን መፈራት በእርሱ ዘንድ ያለ አይደለምን? በከፍታውም ሁሉን ነገር አድራጊ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ገዥነትና ግርማ የእግዚአብሔር ናቸው፤ በሰማይም ከፍታ ሥርዐትን ያደርጋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ገዢነትና መፈራት በእርሱ ዘንድ ናቸው፥ በከፍታውም ሰላምን የሚያሰፍን ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሥልጣንና መፈራት የእግዚአብሔር ነው፤ በላይኛው ግዛቱ በሰማይ ሰላምን ይመሠርታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ገዢነትና መፈራት በእርሱ ዘንድ ናቸው፥ በከፍታውም ሰላም አድራጊ ነው። |
ለዘለዓለም በአርያም የሚኖር ስሙም ቅዱሰ ቅዱሳን የሆነ፥ በቅዱሳን አድሮ የሚኖር፥ ለተዋረዱት ትዕግሥትን የሚሰጥ፥ ልባቸውም ለተቀጠቀጠ ሕይወትን የሚሰጥ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦
ብቻውን ለሆነ አምላክና መድኃኒታችን ከዘመን ሁሉ በፊት አሁንም እስከ ዘላለምም ድረስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ግርማ ኀይልም ሥልጣንም ይሁን፤ አሜን።