Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 16:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 መሬት ሥጋ​ዬን ይሸ​ፍ​ነው ይሆን? ደሜስ ይፈ​ስስ ይሆን? የም​ጮ​ህ​በ​ትስ ቦታ አላ​ገኝ ይሆን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 አሁን እንኳ ምስክሬ በሰማይ አለ፤ ጠበቃዬም በላይ በአርያም ይገኛል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 አሁንም፥ እነሆ፥ ምስክሬ በሰማይ አለ፥ የሚመሰክርልኝም በአርያም ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 እነሆ፥ ለእኔ የሚመሰክርልኝና ጥብቅናም የሚቆምልኝ በሰማይ አለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 አሁንም፥ እነሆ፥ ምስክሬ በሰማይ አለ፥ የሚመሰክርልኝም በአርያም ነው።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 16:19
16 Referencias Cruzadas  

ልጆ​ችን ብት​በ​ድ​ላ​ቸው ወይም በላ​ያ​ቸው ላይ ሚስ​ቶ​ችን ብታ​ገ​ባ​ባ​ቸው እነሆ፥ ከእኛ ጋር ያለ ሰው እን​ደ​ሌለ አስ​ተ​ውል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል ምስ​ክር ነው።”


ነገር ግን በእጄ ዐመፅ የለም፤ ጸሎ​ቴም ንጹሕ ነው።


እኔን ግን የሚ​ቤ​ዠኝ ሕያው እንደ ሆነ፥ በመ​ጨ​ረ​ሻም ዘመን በም​ድር ላይ እን​ዲ​ቆም፥


“ጥን​ቱን መፈ​ራት በእ​ርሱ ዘንድ ያለ አይ​ደ​ለ​ምን? በከ​ፍ​ታ​ውም ሁሉን ነገር አድ​ራጊ ነው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እድል ፋንታ ከላይ፥ ሁሉ​ንም የሚ​ችል የአ​ም​ላክ ርስት ከአ​ር​ያም ምን​ድን ነው?


አንቺ ባሕር የሸ​ሸሽ፥ አን​ተም ዮር​ዳ​ኖስ ወደ ኋላህ የተ​መ​ለ​ስህ፥ ምን ሁና​ችሁ ነው?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከሰ​ማ​ያት አመ​ስ​ግ​ኑት፤ በአ​ር​ያም ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤


ባለ​ማ​ቋ​ረጥ በም​ጸ​ል​የው ጸሎት እን​ደ​ማ​ስ​ባ​ችሁ ልጁ በአ​ስ​ተ​ማ​ረው ወን​ጌል በፍ​ጹም ልቡ​ናዬ የማ​መ​ል​ከው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ክሬ ነው።


በክ​ር​ስ​ቶስ እው​ነት እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሐሰ​ትም አል​ና​ገ​ርም። ሕሊ​ና​ዬም በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ይመ​ሰ​ክ​ር​ል​ናል፤


እኔ ለእ​ና​ንተ በመ​ራ​ራት ወደ ቆሮ​ን​ቶስ እን​ዳ​ል​መ​ጣሁ፥ ስለ ራሴ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምስ​ክር አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።


ለዘ​ለ​ዓ​ለም ቡሩክ አም​ላክ የሆነ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አባት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሐሰት እን​ደ​ማ​ል​ና​ገር ያው​ቃል።


በክ​ር​ስ​ቶስ ፍቅር ሁላ​ች​ሁን እን​ደ​ም​ወ​ዳ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ክሬ ነው።


በእናንተ በምታምኑ ዘንድ እንዴት ባለ ቅድስናና ጽድቅ ነቀፋም በሌለበት ኑሮ እንደ ሄድን፥ እናንተና እግዚአብሔር ምስክሮች ናችሁ፤


እንደምታውቁ፥ እያቈላመጥን ከቶ አልተናገርንም፤ እግዚአብሔርም እንደሚመሰክር እያመካኘን በመጐምጀት አልሠራንም፤


ሳሙ​ኤ​ልም፥ “በእጄ ምንም እን​ዳ​ላ​ገ​ኛ​ችሁ ዛሬ በዚ​ህች ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ክር ነው፤ እርሱ የቀ​ባ​ውም ምስ​ክር ነው” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “አዎ ምስ​ክር ነው” አሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos