ኢዮብ 22:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጻድቃንም አይተው ሳቁ፤ ንጹሓንም በንቀት ይዘባበቱባቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጻድቃንም የእነዚያን ጥፋት አይተው ይደሰታሉ፤ ንጹሓንም እንዲህ ብለው ያፌዙባቸዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህንን አይተው ጻድቃን ደስ ይላቸዋል፥ ንጹሑም ሰው ይስቅባቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉ ሰዎች ሲቀጡ በማየት ደጋግ ሰዎች ይደሰታሉ፤ ቀጥተኞች እንዲህ እያሉ በእነርሱ ላይ ያፌዛሉ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጻድቃን ያዩታል፥ ደስም ይላቸዋል፥ ንጹሐንም በንቀት ይስቁባቸዋል። |
መድኀኒትን ከጽዮን ለእስራኤል ማን ይሰጣል? እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥ ያዕቆብ ደስ ይለዋል እስራኤልም ሐሤትን ያደርጋል።