ኢዮብ 21:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰው የሚዘልፈኝ አይደለም፤ ስለ ምንስ አልቈጣም? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በውኑ ቅርታዬ በሰው ላይ ነውን? ትዕግሥት ማጣትስ አይገባኝምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በውኑ የኀዘን እንጉርጉሮዬን ለሰው እናገራለሁን? አለመታገሤ ተገቢ አይደለምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እኔ የማዝነው በሰብአዊ ፍጡር ላይ ነውን? ታዲያ፥ ትዕግሥቴ ቢያልቅ ምን ያስገርማል? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ የኅዘን እንጕርጕሮዬ ለሰው እናገራለሁን? አለመታገሥ ስለ ምን አይገባኝም? |
ሙሴም ይህን ለእስራኤል ልጆች ተናገረ፤ እነርሱ ግን ከሰውነታቸው መጨነቅ፥ ከሥራቸውም ክብደት የተነሣ ቃሉን አልሰሙትም።