ኢዮብ 19:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ እግዚአብሔር እንደ አወከኝ፥ መዓቱንም በእኔ ላይ እንደ አበዛ ዕወቁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እንደ በደለኝ፣ በመረቡም እንደ ከበበኝ ዕወቁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ እግዚአብሔር ጥፋተኛ እንዳደረገኝ፥ በመረቡም እንደ ከበበኝ እወቁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ይህን ሁሉ መከራ ያደረሰብኝና መረብ ውስጥም የጣለኝ እግዚአብሔር መሆኑን እንድታውቁ እወዳለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ እግዚአብሔር እንደ ገለበጠኝ፥ በመረቡም እንደ ከበበኝ እወቁ። |
የሰውን ልብ፦ የምታውቅ ሆይ፥ በድዬስ እንደ ሆነ እንግዲህ ምን ላደርግልህ እችላለሁ? ስለምን እኔን ለመከራ አደረግኸኝ? ስለ ምን በአንተ ላይ እንድናገር በአምሳልህ ፈጠርኸኝ? ስለ ምንስ እኔ ሸክም ሆንሁብህ?
መረቤንም በእርሱ ላይ እዘረጋለሁ፤ በወጥመዴም ይያዛል፤ ወደ ከለዳውያንም ምድር ወደ ባቢሎን አመጣዋለሁ፤ ሆኖም አያያትም፤ በዚያም ይሞታል።
ሲሄዱም አሽክላዬን እዘረጋባቸዋለሁ፤ እንደ ሰማይ ወፎችም አወርዳቸዋለሁ፤ መከራቸውን ሲሰሙ እገሥጻቸዋለሁ።