ኢዮብ 16:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ለጠማማ ሰው አሳልፎ ሰጠኝ፤ በክፉዎችም እጅ ጣለኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሰላም እኖር ነበር፤ እርሱ ግን ሰባበረኝ፤ ዐንገቴን ይዞ አደቀቀኝ፤ ማነጣጠሪያ ዒላማው አደረገኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በርጋታ ተቀምጬ ነበር፥ እርሱም ሰበረኝ፥ አንገቴንም ይዞ ቀጠቀጠኝ፥ እንደ ዒላማ አድርጎ አቆመኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሰላም እኖር ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በቊጣው ሰባበረኝ፤ አንገቴንም አንቆ ፈጠፈጠኝ፤ ለዒላማውም አደረገኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተዘልዬ ተቀምጬ ነበር፥ እርሱም ሰበረኝ፥ አንገቴንም ይዞ ቀጠቀጠኝ፥ እንደ ዓላማ አድርጎ አቆመኝ። |
የሰውን ልብ፦ የምታውቅ ሆይ፥ በድዬስ እንደ ሆነ እንግዲህ ምን ላደርግልህ እችላለሁ? ስለምን እኔን ለመከራ አደረግኸኝ? ስለ ምን በአንተ ላይ እንድናገር በአምሳልህ ፈጠርኸኝ? ስለ ምንስ እኔ ሸክም ሆንሁብህ?
በእጅ በያዙህ ጊዜ ተሰበርህ፤ ጫንቃቸውንም ሁሉ አቈሰልህ፤ በተደገፉብህም ጊዜ ተሰበርህ፤ ወገባቸውንም ሁሉ አንቀጠቀጥህ።
ስለ እኔ ሰውነታቸውን ለመከራ አሳልፈው ሰጥተዋልና፤ የማመሰግናቸውም እኔ ብቻ አይደለሁም፤ ከአሕዛብ ያመኑ ምእመናን ሁሉ ያመሰግኑአቸዋል እንጂ።