Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 16:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በርጋታ ተቀምጬ ነበር፥ እርሱም ሰበረኝ፥ አንገቴንም ይዞ ቀጠቀጠኝ፥ እንደ ዒላማ አድርጎ አቆመኝ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 በሰላም እኖር ነበር፤ እርሱ ግን ሰባበረኝ፤ ዐንገቴን ይዞ አደቀቀኝ፤ ማነጣጠሪያ ዒላማው አደረገኝ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 በሰላም እኖር ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በቊጣው ሰባበረኝ፤ አንገቴንም አንቆ ፈጠፈጠኝ፤ ለዒላማውም አደረገኝ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለጠ​ማማ ሰው አሳ​ልፎ ሰጠኝ፤ በክ​ፉ​ዎ​ችም እጅ ጣለኝ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ተዘልዬ ተቀምጬ ነበር፥ እርሱም ሰበረኝ፥ አንገቴንም ይዞ ቀጠቀጠኝ፥ እንደ ዓላማ አድርጎ አቆመኝ።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 16:12
19 Referencias Cruzadas  

በደንዳና አንገቱና በወፍራሙ ጋሻው እየገሠገሠ ወደ እርሱ ይመጣበታልና፥


እግዚአብሔር ለጠማማ ሰው አሳልፎ ሰጠኝ፥ በክፋዎችም እጅ ጣለኝ።


እግዚአብሔር ልቤን አባብቶታልና፥ ሁሉንም የሚችል አምላክ አስደንግጦኛል።


በራሴ ላይ መብራቱ በበራ ጊዜ፥ እኔም ጨለማውን አልፌ በብርሃኑ በሄድሁ ጊዜ፥


ተዘልዬ አልተቀመጥሁም፥ አልተማመንሁም፥ አላረፍሁም፥ ነገር ግን መከራ መጣብኝ።”


የአንበሳ ጩኸት፥ የጩዋኺ አንበሳ ድምፅ፥ የአንበሳ ደቦል ጥርስ ተሰባበረ።


ሁሉን የሚችል የአምላክ ፍላጻ በሥጋዬ ውስጥ ነው፥ መርዙንም ነፍሴ ትጠጣለች፥ የእግዚአብሔር ሽብሮች በኔ ላይ ተሰልፈዋል።


እኔ ባሕር ነኝ ወይስ ዓሣ አንበሪ? ባላዬ ጠባቂ የምታኖርብኝ?


ሰውን የምትጠብቅ ሆይ፥ በድዬስ እንደሆነ ምን ላድርግልህ? ስለምን እኔን ዒላማ አደረግኸኝ? ስለምን እኔ ሸክም ሆንሁብህ?


በዐውሎ ነፋስ ይሰብረኛል፥ ቁስሌንም ያለ ምክንያት ያበዛል።


ልባችን ወደ ኋላው አልተመለሰም፥ ፍለጋችንም ከመንገድህ ፈቀቅ አላለም፥


ዘወትር ቀኑን ሁሉ እጁን በላዬ መለሰ።


ቤት። ሥጋዬንና ቁርበቴን አስረጀ፥ አጥንቴን ሰበረ።


በእጅህ በያዙህ ጊዜ ተሰበርህ ትከሻቸውን ሁሉ ቆረጥህ፤ በአንተ ላይ ሲደገፉ ተሰበርህ ወገባቸውንም ሁሉ አንቀጠቀጥህ።”


በዚህ ድንጋይ ላይ የሚወድቅ ይሰባበራል፤ ድንጋዩ በላዩ ላይ የሚወድቅበትን ሁሉ ግን ያደቅቀዋል።”


እነርሱም ስለ እኔ ነፍስ ሲሉ አንገታቸውን አደጋ ላይ ጣሉ፤ እነርሱንም እኔ ብቻ ሳልሆን የአሕዛብም አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ያመሰግኗቸዋል፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos