ኢዮብ 15:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚፈርድብህ አፍህ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም፤ ከንፈሮችህም ይመሰክሩብሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚፈርድብህ አንደበትህ እንጂ እኔ አይደለሁም፣ የሚመሰክርብህም እኔ ሳልሆን የገዛ ከንፈርህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚፈርድብህ አፍህ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም፥ ከንፈሮችህም ይመሰክሩብሃል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚፈርድብህ የገዛ አንደበትህ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም፤ አነጋገርህም ያጋልጥሃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚፈርድብህ አፍህ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም፥ ከንፈሮችህም ይመሰክሩብሃል። |
ምክርን ከአንተ የሚሰውር፥ ቃሉንም ከአንተ የሚሸልግና የሚሸሽግ የሚመስለው ማን ነው? የማላስተውለውንና የማላውቀውንም ታላቅና ድንቅ ነገር የሚነግረኝ ማን ነው?
በዚያን ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ልብሱን ቀዶ “ተሳድቦአል፤ እንግዲህ ወዲህ ምስክሮች ስለ ምን ያስፈልገናል? እነሆ፥ ስድቡን አሁን ሰምታችኋል፤ ምን ይመስላችኋል?” አለ።
ጌታውም እንዲህ አለው፦ አንተ ክፉ ሰነፍ አገልጋይ፥ እኔ ያላስቀመጥሁትን የምወስድ፥ ያልዘራሁትን የማጭድ፥ ያልበተንሁትንም የምሰበስብ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንሁ ታውቃለህን? እንደ ቃልህ እፈርድብሃለሁ።