እርስዋም ኤልያስን፥ “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ እኔ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? አንተስ ከእኔ ጋር ምን አለህ? ኀጢአቴንስ ታሳስብ ዘንድ፥ ልጄንስ ትገድል ዘንድ ወደ እኔ መጥተሃልን?” አለችው።
ኢዮብ 13:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክፉ ነገርን ጽፈህብኛልና፤ የልጅነቴንም ኀጢአት ተቈጣጥረህ አስታጥቀኸኛልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መራራ ነገር ትጽፍብኛለህ፤ የወጣትነቴንም ኀጢአት ታወርሰኛለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመረረ ነገር ጽፈሕብኛልና፥ የልጅነቴንም ኃጢአት ታወርሰኛለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በእኔ ላይ የጻፍከው ክስ እጅግ መራራ ነው፤ በልጅነቴ የሠራሁትን በደል እንኳ አልተውክልኝም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የመረረ ነገር ጽፈህብኛልና፥ የሕፃንነቴንም ኃጢአት ታወርሰኛለህ። |
እርስዋም ኤልያስን፥ “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ እኔ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? አንተስ ከእኔ ጋር ምን አለህ? ኀጢአቴንስ ታሳስብ ዘንድ፥ ልጄንስ ትገድል ዘንድ ወደ እኔ መጥተሃልን?” አለችው።
ከተመለስሁ በኋላ ተጸጸትሁ፤ ከተገሠጽሁም በኋላ ጭኔን ጸፋሁ፤ የብላቴንነቴንም ስድብ ተሸክሜአለሁና አፈርሁ፥ ተዋረድሁም።
ከዚህም በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ያን የዳነውን ሰው በቤተ መቅደስ አገኘውና፥ “እነሆ፥ ድነሃል፤ ግን ከዚህ የባሰ እንዳያገኝህ ዳግመኛ እንዳትበድል ተጠንቀቅ” አለው።