Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዮሐንስ 5:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ያን የዳ​ነ​ውን ሰው በቤተ መቅ​ደስ አገ​ኘ​ውና፥ “እነሆ፥ ድነ​ሃል፤ ግን ከዚህ የባሰ እን​ዳ​ያ​ገ​ኝህ ዳግ​መኛ እን​ዳ​ት​በ​ድል ተጠ​ን​ቀቅ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ያን ሰው በቤተ መቅደስ አግኝቶ፣ “እነሆ፣ ተፈውሰሃል፤ ከእንግዲህ ግን ኀጢአት አትሥራ፤ አለዚያ ከዚህ የባሰ ይደርስብሃል” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በቤተ መቅደስ አገኘውና “እነሆ፥ ድነሃል፤ ከዚህ የሚብስ እንዳይደርስብህ ወደ ፊት ኃጢአት አትሥራ፤” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ሰውየውን በቤተ መቅደስ አገኘውና “እነሆ፥ አሁን ድነሃል፤ ከዚህ የባሰ ነገር እንዳይደርስብህ ከእንግዲህ ወዲህ ኃጢአት አትሥራ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በመቅደስ አገኘውና፦ እነሆ፥ ድነሃል፤ ከዚህ የሚብስ እንዳይደርስብህ ወደ ፊት ኃጢአት አትሥራ አለው።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 5:14
23 Referencias Cruzadas  

እር​ስ​ዋም፥ “ጌታ ሆይ፥ የማ​የው የለም” ብላ መለ​ሰ​ች​ለት፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እኔም አል​ፈ​ር​ድ​ብ​ሽም፤ ወደ ቤትሽ ሂጂ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ዳግ​መኛ ኀጢ​ኣት አት​ሥሪ” አላት።


ዓይ​ኖ​ችን ክፈት፥ ከሕ​ግ​ህም ድንቅ ነገ​ርን አያ​ለሁ።


ባረ​ፉም ጊዜ ተመ​ል​ሰው በፊ​ትህ ክፉ አደ​ረጉ፤ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም እጅ ተው​ሃ​ቸው፤ ገዙ​አ​ቸ​ውም፤ ተመ​ል​ሰ​ውም ወደ አንተ በጮኹ ጊዜ ከሰ​ማይ ሰማ​ሃ​ቸው፤ እንደ ምሕ​ረ​ት​ህም ብዛት ታደ​ግ​ሃ​ቸው፤


ከዚያ ወዲያ ይሄድና ከእርሱ የከፉትን ሰባት ሌሎችን አጋንንት ከእርሱ ጋር ይወስዳል፤ ገብተውም በዚያ ይኖራሉ፤ ለዚያም ሰው ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛው ይብስበታል። ለዚህ ክፉ ትውልድ ደግሞ እንዲሁ ይሆንበታል።”


እስ​ከ​ዚ​ህም ድረስ ባት​ሰ​ሙኝ፥ አግ​ድ​ማ​ች​ሁም ብት​ሄ​ዱ​ብኝ፥


ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን “አንተ ልጅ! ኀጢአትህ ተሰረየችልህ፤” አለው።


ጌታዬ ሆይ አንተ መድ​ኀ​ኒቴ ነህ፤ ስለ​ዚህ በሕ​ይ​ወቴ ዘመን ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አው​ታር ባለው ዕቃ አን​ተን ማመ​ስ​ገ​ንን አላ​ቋ​ር​ጥም።”


የል​መ​ና​ዬን ቃል ሰም​ቶ​ኛ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።


በዚ​ያም ከታ​መመ ሠላሳ ስም​ንት ዓመት የሆ​ነው አንድ ሰው ነበር።


ዳግ​መ​ኛም ንጉሡ አካዝ ፈጽሞ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራቀ።


አቤቱ፥ ይቅር በለኝ፥ ጠላ​ቶቼም የሚ​ያ​መ​ጡ​ብ​ኝን መከራ እይ፥ ከሞት ደጆች ከፍ ከፍ የሚ​ያ​ደ​ር​ገኝ፤


የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና።


ለም​ስ​ጋና ቢያ​ቀ​ር​በው፥ ከም​ስ​ጋ​ናው መሥ​ዋ​ዕት ጋር በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ የቂጣ እን​ጎቻ፥ በዘ​ይ​ትም የተ​ቀባ ስስ ቂጣ፥ በዘ​ይ​ትም የተ​ለ​ወሰ መል​ካም የስ​ንዴ ዱቄት ያቀ​ር​ባል።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም፥ “ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እወጣ ዘንድ ምል​ክቱ ምን​ድን ነው?” ብሎ ነበር።


ያ የተ​ፈ​ወ​ሰው ግን ያዳ​ነው ማን እንደ ሆነ አላ​ወ​ቀም፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በዚያ ቦታ በነ​በ​ሩት ብዙ ሰዎች መካ​ከል ተሰ​ውሮ ነበ​ርና።


ካህ​ኑም ያያል፤ እነ​ሆም፥ ወደ ቆዳው ውስጥ ጠልቆ ቢታይ፥ ጠጕ​ሩም ተለ​ውጦ ቢነጣ፥ ካህኑ፦ ‘ርኩስ ነው’ ይለ​ዋል፤ የለ​ምጽ ደዌ ነው፤ ከቍ​ስሉ ውስጥ ወጥ​ቶ​አል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios