ኢዮብ 10:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዘለዓለም ጨለማም ወደ አለባት፥ ብርሃንም ወደሌለባት፥ ማንም የሟችን ሕይወት ወደማያይባት ምድር ሳልሄድ ጥቂት አርፍ ዘንድ ተወኝ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብርሃኑ እንደ ጨለማ ወደ ሆነበት፣ የሞት ጥላ ወዳረበበበት፣ ሥርዐት የለሽ ወደ ሆነ ምድር፣ ድቅድቅ ጨለማ ወደ ሰፈነበት አገር ሳልሄድ ተወኝ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ጨለማም ወደ ጨለመች፥ ሥርዓትም ወደሌለባት ወደ ሞት ጥላ፥ ብርሃንዋም እንደ ጨለማ ወደ ሆነ ምድር ሳልሄድ፥ ጥቂት እጽናና ዘንድ ተወኝ፥ ልቀቀኝም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምሄድበት ስፍራ የጨለማ ጥላና ሁከት የተሞላበት ምድር ነው፤ በዚያም ያለው ብርሃን እንደ ጨለማ ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ ጨለማም ወደ ጨለመች፥ ሥርዓትም ወደሌለባት ወደ ሞት ጥላ፥ ብርሃንዋም እንደ ጨለማ ወደ ሆነ ምድር ሳልሄድ፥ ጥቂት እጽናና ዘንድ ተወኝ፥ ልቀቀኝም። |
አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና ዐሳብ፥ ዕውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምትችለውን ሁሉ እንደ ኀይልህ አድርግ።
ሳይጨልምባችሁ፥ ጨለማም ባለባቸው ተራሮች እግሮቻችሁ ሳይሰነካከሉ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ፤ በዚያም የሞት ጥላ አለና በጨለማውም ውስጥ ያኖራችኋልና ብርሃንን ተስፋ ታደርጋላችሁ።
እነርሱም፥ “ከግብፅ ምድር ያወጣን፥ በምድረ በዳና በባድማ፥ ዕንጨትና ውኃ፥ የእንጨት ፍሬም በሌለበት ምድር፥ ሰው በማያልፍበትና የሰው ልጅም በማይቀመጥበት ምድር የመራን እግዚአብሔር ወዴት አለ? አላሉም።
ከዚህም ሁሉ ጋር ከዚህ ወደ እናንተ ማለፍ የሚሹ እንዳይችሉ፥ ከእናንተ ወገን የሆኑትም ወደ እኛ እንዳይሻገሩ በእኛና በእናንተ መካከል ታላቅ ገደል አለ’