La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢዮብ 10:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዲህ እለ​ዋ​ለሁ፦ ኀጢ​ኣ​ተኛ እን​ድ​ሆን አታ​ስ​ተ​ም​ረኝ፤ ለም​ንስ እን​ደ​ዚህ ፈረ​ድ​ህ​ብኝ?

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔርን እንዲህ እለዋለሁ፤ በምን ላይ እንዳልተስማማን ንገረኝ እንጂ አትፍረድብኝ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እግዚአብሔርን እንዲህ እለዋለሁ፦ አትፍረድብኝ፥ የምትከራከረኝ ለምን እንደሆነ ንገረኝ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔርን እንዲህ እለዋለሁ፦ በእኔ ላይ ያለህን ቅርታ ግለጥልኝ እንጂ አትፍረድብኝ!

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔርን እንዲህ እለዋለሁ፦ አትፍረድብኝ፥ የምትከራከረኝ ለምን እንደ ሆነ ንገረኝ።

Ver Capítulo



ኢዮብ 10:2
20 Referencias Cruzadas  

ኀጢ​አ​ቶ​ችና በደሌ ምን ያህል ናቸው? ምን ያህል እንደ ሆኑ አስ​ታ​ው​ቀኝ።


ሰው የሚ​ዘ​ል​ፈኝ አይ​ደ​ለም፤ ስለ ምንስ አል​ቈ​ጣም?


አንተ፦ ‘ቃሌን ሁሉ ለምን አይ​ሰ​ማ​ኝም?’ ትላ​ለህ።


“በውኑ የሚ​ከ​ራ​ከር ሰው ሁሉን ከሚ​ችል አም​ላክ ጋር ይከ​ራ​ከ​ራ​ልን? ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር የሚ​ዋ​ቀስ እርሱ ይመ​ል​ስ​ለት።”


የሰ​ውን ልብ፦ የም​ታ​ውቅ ሆይ፥ በድ​ዬስ እንደ ሆነ እን​ግ​ዲህ ምን ላደ​ር​ግ​ልህ እች​ላ​ለሁ? ስለ​ምን እኔን ለመ​ከራ አደ​ረ​ግ​ኸኝ? ስለ ምን በአ​ንተ ላይ እን​ድ​ና​ገር በአ​ም​ሳ​ልህ ፈጠ​ር​ኸኝ? ስለ ምንስ እኔ ሸክም ሆን​ሁ​ብህ?


“ኃጢ​ኣ​ተኛ ሰው ከሆ​ንሁ፤ ስለ ምን አል​ሞ​ት​ሁም?


ከእ​ርሱ ጋር ይከ​ራ​ከር ዘንድ ቢወ​ድድ፥ ከሺህ ነገር አን​ዱን መመ​ለስ አይ​ች​ልም።


የሚ​ም​ረኝ፥ መሸ​ሸ​ጊ​ያዬ፥ መጠ​ጊ​ያ​ዬና አዳኜ፤ መታ​መ​ኛ​ዬም፤ እር​ሱን ታመ​ንሁ፤ ሕዝ​ቡ​ንም ከእኔ በታች የሚ​ያ​ስ​ገ​ዛ​ልኝ።


የም​ስ​ጋ​ና​ህን ቃል እሰማ ዘንድ፥ ተአ​ም​ራ​ት​ህ​ንም ሁሉ እነ​ግር ዘንድ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረዳ​ቴና መታ​መ​ኛዬ ነው፤ ልቤ በእ​ርሱ ታመነ፥ እር​ሱም ይረ​ዳ​ኛል፤ ሥጋ​ዬም ለመ​ለመ፥ ፈቅ​ጄም አም​ነ​ዋ​ለሁ።


እን​ግ​ዲህ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ላሉት በመ​ን​ፈስ እንጂ በሥጋ ለማ​ይ​መ​ላ​ለሱ ፍርድ የለ​ባ​ቸ​ውም።