La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 7:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከግ​ብፅ ምድር ባወ​ጣ​ኋ​ችሁ ቀን ስለ​ሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትና ስለ ቍር​ባን ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አል​ተ​ና​ገ​ር​ሁ​ምና፥ አላ​ዘ​ዝ​ኋ​ቸ​ው​ምም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የቀድሞ አባቶቻችሁን ከግብጽ ባወጣኋቸው ጊዜ፣ ስለ መሥዋዕቶችና ስለሚቃጠል መሥዋዕት አልተናገርኋቸውም፤ ትእዛዝም አልሰጠኋቸውም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከግብጽ ምድር ባወጣኋችሁ ቀን ስለሚቃጠል መሥዋዕትና ስለ ሌላ መሥዋዕት ለአባቶቻችሁ አልተናገርሁምና፥ አላዘዝኋቸውምም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የቀድሞ አባቶቻችሁን ከግብጽ ባወጣኋቸውም ጊዜ ስለሚቃጠልም ሆነ ስለ ሌላው ዐይነት መሥዋዕት ምንም ትእዛዝ አልሰጠኋቸውም፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከግብጽ ምድር ባወጣኋችሁ ቀን ስለሚቃጠል መሥዋዕትና ስለ ሌላ መሥዋዕት ለአባቶቻችሁ አልተናገርሁምና፥ አላዘዝኋቸውምም።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 7:22
9 Referencias Cruzadas  

ከን​ቱን የሚ​ና​ገር ይግ​ባና ይይ፤ ልቡ በላዩ ላይ ኀጢ​አ​ትን ሰበ​ሰበ፤ ወደ ሜዳ ይወ​ጣል ይና​ገ​ራ​ልም፥ በእ​ኔም ላይ ይተ​ባ​በ​ራል።


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችና የይ​ሁዳ ልጆች ከታ​ና​ሽ​ነ​ታ​ቸው ጀምሮ በፊቴ ክፉ ነገ​ርን ብቻ አድ​ር​ገ​ዋ​ልና፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እኔን በእ​ጃ​ቸው ሥራ ከማ​ስ​ቈ​ጣት በቀር ሌላ ሥራ አላ​ደ​ረ​ጉ​ምና፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ከመ​ሥ​ዋ​ዕት ይልቅ ምሕ​ረ​ትን፥ ከሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት ይልቅ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማወቅ እወ​ድ​ዳ​ለ​ሁና።


ነገር ግን ሄዳችሁ ‘ምሕረትን እወዳለሁ መሥዋዕትንም አይደለም፤’ ያለው ምን እንደ ሆነ ተማሩ፤ ኀጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁምና፤” አላቸው።


በፍጹም ልብ በፍጹም አእምሮም በፍጹም ነፍስም በፍጹም ኀይልም እርሱን መውደድ፥ ባልንጀራንም እንደ ራስ መውደድ በሙሉ ከሚቃጠል መሥዋዕትና ከሌላው መሥዋዕት ሁሉ የሚበልጥ ነው፡” አለው።


ሄዶም ሌሎች አማ​ል​ክ​ትን ያመ​ለከ፥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላላ​ዘ​ዘህ ለፀ​ሐ​ይና ለጨ​ረቃ ወይም ለሰ​ማይ ከዋ​ክ​ብት የሰ​ገደ ቢገኝ፥


ሳሙ​ኤ​ልም ሳኦ​ልን፥ “በውኑ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል በመ​ስ​ማት ደስ እን​ደ​ሚ​ለው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ቃ​ጠ​ልና በሚ​ታ​ረድ መሥ​ዋ​ዕት ደስ ይለ​ዋ​ልን? እነሆ፥ መታ​ዘዝ ከመ​ሥ​ዋ​ዕት፥ ማዳ​መ​ጥም የአ​ውራ በግ ስብ ከማ​ቅ​ረብ ይበ​ል​ጣል።